አሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይን ዋና አሰልጣኝ አድርገዉ ከሾሙ በኋላ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት ብርቱካናማዎቹ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ሶስት ተጫዋቾችን ማስፈረማቸዉን ይፋ አድርገዋል።
የመጀመሪያው ፈራሚ የዉድድር አመቱን በአዲስ አበባ ከተማ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ የቀኝ መስመር ተከላካዩ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ እንደ አሰጋኸኝ ሁሉ ዉድድር አመቱን በአዲስ አበባ ከተማ ያሳለፈዉ አጥቂዉ ቢኒያም ጌታቸዉ ሆኗል።
በሶስተኝነት ማረፊያውን ድሬዳዋ ከተማ ያደረገዉ ደግሞ ከዚህ ቀደም ለቡራዩ ከተማ መጫወት የቻለዉ እና የተጠናቀቀዉን ግማሽ አመት በጂማ አባጅፋር ቤት ያሳለፈዉ ሁለገቡ ተጫዋች ጫላ በንቲም ሆኗል።