ከሰዓታት በፊት ሀድያ ሆሳዕና የነባር ተጫዋቹን ግርማ በቀለን ዉል ማደሱን እንዲሁም የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነዉን ዳግም ንጉሴን ማስፈረማቸዉን አጋርተናችሁ ነበር አሁን ደግሞ የመስመር ተጫዋቹን ቤዛ መድንን ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
በተጠናቀቀዉ የዉድድር አመት በክትፎዎቹ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ እና ከዚህ ቀደም ለኢኮስኮ ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ እና ገላን ከተማ መጫወት የቻለዉ የመስመር ተጫዋቹ በዛሬዉ ዕለት ሌላኛዉን የክለብ አጋሩን ተከትሎ ለሀድያ ሆሳዕና ለመጫወት ፊርማውን ማኖሩን ክለቡ ይፋ አድርጓል።