በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት መከላከያዎች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የመስመር ተከላካዩን አህመድ ረሽድን ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ረዘም ላሉ አመታት ለኢትዮጵያ ቡና እና መጫወት የቻለዉ እና ያለፉትን ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ቆይታ የነበረዉ ተጫዋቹ ሁለት አመት በሚቆይ ዉል ለመከላከያ መፈረሙ ተረጋግጧል።