አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመን ዋና አሰልጣኝ አድርገዉ ከሾሙ በኋላ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ዛሬ ከሰዓት ደግሞ አበባየሁ ዮሐንስን ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለደቡብ ፖሊስ ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ያለፈዉን አንድ አመት ለሀድያ ሆሳዕና መጫወት የቻለዉ አማካዩ በድጋሚ ወደ ቀድሞ ቤቱ የሚመልሰውን ዝዉዉር ዛሬ ከሰዓት አጠናቋል።