ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምሰት አመታት በኋላ የሊጉ ሻምፕየን መሆን ሲችል ለውጤቱ ጉልህ ሚና ከተወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ አማኑኤል ገብረሚካኤል እንደነበር ይታወሳል ።
ተጫዋቹ ከውድድር አመቱ መጠናቀቅ በኋላ ግን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለቡ እንደተለያየ እና በተለይም ወደ ግብፅ ሊግ ሊያመራ እንደሚችል በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል ።
ነገር ግን ተጫዋቹ የዝውውር ሂደቱ አለመሳካቱን ተከትሎ የውድድር ዓመቱን በፈረሰኞቹ ቤት ለመቆየት መስማማቱ ተሰምቷል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን የፊታችን ቅዳሜ 7:00 ላይ ከኢትዮጵያ መድኅን ጋር የሚያደርግ ይሆናል ።