” እስከአሁን 11 ጨዋታዎችን አልተሸነፍንም ”
” ለኮስታሪካዉ የአለም ዋንጫ ለማለፍ ነዉ ጥረታችን ”
ፍሬዉ ሀይለገብኤል የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ
በዛሬዉ ዕለት የቦትስዋና አቻቸዉን በደርሶ መልስ 8ለ1 አሸንፈዉ ወደ ቀጣዩ ዙር የተቀላቀሉት የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ፍሬዉ ሀይለገብርኤል ከጨዋታው መጠናቀቅ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥቷል።
- ማሰታውቂያ -
° በዉጤቱ ተደስቻለሁ ጨዋታዉንም እንዳያችሁት የተሻለ ነገር ማሳየት ችለናል። ነገር ግን በአጨራረስ ረገድ አሁንም ማሻሻል ያሉብን ነገሮች አሉ ፤ ያዉ ታዳጊዎችም ስለሆኑ በስራ የሚሻሻል እና የሚስተካከል ይሆናል።
° በምንፈልገው መንገድ መጫወታችንም ቡድኑ ምን አይነት መንገድ ይዞ እየተጓዘ እንዳለ እያስመለከተን ነዉ ብየ አስባለሁ።
° ሌላኛዉ በዛሬው ጨዋታ ላይ ከሜዳችን ዉጭ ከነበረን በተለየ መልኩ ታዳጊዎቻችንን ቀይረን ወደ ሜዳ በማስገባት የኢንተርናሽናል ጨዋታ ልምድ እንዲያገኙ አድርገናል።
° ዛሬ 11ኛ ጨዋታችንን ነዉ ያደረግነዉ እስከ አሁን አንድም ሽንፈት አልገጠመንም ይሄ በጣም አሪፍ ልምድ እንድናገኝ ረድቶናል።
° በቀጣይ ከታንዛኒያ እና ቡርንዲ የሚያልፈውን ቡድን አይተን የዝግጅታችንን ሁኔታ እንወስናለን
° ዕቅዳችን ኮስታሪካ ለመሄድ ነዉ በተጫዋቾቼ ሙሉ ዕምነት አለኝ በፌደሬሽኑ በኩልም ጥሩ ድጋፍ ነዉ የሚደረግልን ፤ ህዝብም እስከአሁን እንደነበረዉ ድጋፉን አጠናክሮ እንደቀጥልልን እላለሁ።