የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ከሳምንታት በፊት አሰልጣኝ ሚሉቲን ሰርጆቪች ሚቾን ዋና አሰልጣኝ አድርገው መሾማቸው ይታወሳል።
በዛሬው እለት ደግሞ አሰልጣኝ ሚቾ በይፋ ፊርማውን ሲያኖር የአሰልጣኝ ክፍል አባላቱንም አሳውቋል። ይህንንም ተከትሎ በበሳል ትንትናዎቹ የሚታወቀው እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ረዘም ላሉ አመታት ሲሰራ የቆየው አዲስ ወርቁ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን የቪድዮ አናሊስት ሆኖ መሾሙ ታዉቋል።
ከ2010 አመት አንስቶ ከፈረሰኞቹ ጋር መስራት የጀመረዉ አዲስ ወርቁ ከተለያዩ የዉጭ ሀገር አሰልጣኞች ጋርም አብሮ በመስራት ከፍተኛ ልምድን አግኝቷል። በተለይ ደግሞ ከዚህ ቀደም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በነበራቸው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ በመገኘት የቪዲዮ አናሊስስ መስራቱ ይታወቃል። ለአብነትም የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድንን እና የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድንን ጨዋታዎች በአካል በመገኘት የቪዲዮ አናሊስስ መስራት ችሏል።
በዛሬዉ ዕለት ደግሞ የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ክፍል አባል መሆኑ ታዉቋል።