ለግብፁ ኤል ጉና ክለብ የሚጫወተው የዋልያዎቹ ቁልፍ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ በትላንትናው ዕለት ወደ ባህርዳር በመግባት ብሄራዊ ቡድኑን የተቀላቀለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከቡድኑ ጋር የመጀመሪያ ልምምዱን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።
ለ2022 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምድቡን ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ የምድቡ መሪ ከሆነችው ሀገር ደቡብ አፍሪካ ጋር በመጪው መስከረም 29 እና ጥቅምት 2 የሚያደርግ ሲሆን ለነዚህ ሁለት ጨዋታዎችም 25 ተጨዋቾችን በመጥራት በባህርዳር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል ።
24 ተጨዋቾች በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ መሆኑን ተከትሎ ከቀናት በፊት ወደ ባህር ዳር በማቅናት ዝግጅታቸውን እያደረጉ የነበረ ሲሆን በግብፅ ሊግ ለኤል ጉና የሚጫወተው የብሄራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ በትላንትናው ዕለት ቡድኑን ተቀላቅሏል ። ተጫዋቹም በዛሬው ዕለት ከቡድኑ ጋር የመጀመሪያ ልምምዱን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።