የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅታቸውን ታህሳስ 16 እንደሚጀምሩ መገለፁ ይታወሳል። ከዚህ ባሻገር ዝግጅታቸውን በሀገር ውስጥ ወይስ ከሀገር ዉጭ ያደርጋሉ የሚለዉ ጥያቄ በብዙ የስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ሲጠበቅ ቆይቷል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ብሔራዊ ቡድኑ ከሀገር ወጥቶ ዝግጅቱን እንዲያደርግ እና አስፈላጊውን ወጪ የሚመለከተዉ የመንግስ አካል እንዲሸፍን ከባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ጋር መምከራቸውን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን በተሰማዉ ዜና ደግሞ ዋልያዎቹ ዝግጅታቸውን የአፍሪካ ዋንጫው በሚደረግባት ካሜሩን እንደሚያደርጉ ዕርግጥ ሆኖአል።
በአሁኑ ሰዓት በሀዋሳ ከተማ የየክለብ ግዳጃቸዉን እየተወጡ የሚገኙት ተጫዋቾቹ ታህሳስ 14 የፕሪሚየር ሊግ ዉድድራቸዉን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ አዲስአበባ በማምራት በመሰባሰብ ታህሳስ 16 ወይም 17 ወደ ስፍራው ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።