➢የሊጉም መጀመሪያ ቀን መራዘሙ አይቀርም ተብሏል…
ዋሊያዎቹ ከማላዊና ግብጽ አቻዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት የጨዋታ ቀናቶች ጭማሪ እንደተረገባቸው ካፍ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ካፍን ጠቅሶ እንደገለጸው ግንቦት 25 እና 29 ዋሊያዎቹ ከማላዊና ግብጽ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ግንቦት 28 እና ሰኔ 2/2014 እንዲካሄድ መወሰኑ ታውቋል።
ዋሊያዎቹ ከነዚህ የማጣሪያ ጨዋታዎች አስቀድሞ ከሌሴቶ አቻቸው ጋር በቀናት ልዩነት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ቆይታቸውን በጁፒተር ሆቴል አድርገው ዝግጅታቸውን ይቀጥላሉ ቸብሎ ይጠበቃል።
- ማሰታውቂያ -
ይህን ተከትሎ ሰኔ 4 /2014 ሊጀመር የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃግብር ለቀናቶች እንደሚራዘም ይጠበቃል።