የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሀል ሜዳ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ ዛሬ ጠዋት ባህርዳር አየር ማረፊያ የደረሰ ሲሆን፣አቫንቲ ብሉናይል የሚገኘዉን የዋልያዎቹ ስብስብ እንደተቀላቀለም ታዉቋል።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ላለባት ሁለት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ጨዋታዎች በአሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጨዋቾች መካከል ከንዱ የሆነዉ አማካዩ ሽመልስ በቀለ ዛሬ ከሰዓት በሚደረገዉ የዋልያዎቹ እና የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚገኝ ይጠበቃል።
በግብፅ ሊግ ላይ ማንፀባረቅ የቻለዉ ሽመልስ ባሳለፍነዉ ሳምንት ለክለቡ ግሩም ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል። በዚህም አማካዩ በዉድድር አመቱ በግብፅ ሊግ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ አስራ አንድ ከፍ ማድረግ ችሏል።