በ2023 ለሚደረገዉ የኮትዲቫር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸዉን እያደረጉ የሚገኙት ዋልያዎቹ ከዕሁዱ የማላዊ ሽንፈት በኋላ በትላንትናው ዕለት ልምምዳቸውን አከናውነዋል።
በምድባቸዉን ሁለተኛ ጨዋታ የፊታችን ሀሙስ ምሽት 1ሰዓት ላይ በማላዊ ቤንጉ ስታዲየም ከግብፅ ብሐራዊ ቡድን ጋር የሚያደርጉት ዋልያዎቹ በጉዳት ምክንያት የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ግልጋሎት የማግኘታቸው ነገር አጠራጣሪ ሆኖአል።
የተከላካዩ መስመር ተጫዋቹ ያሬድ ባየ እና አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸዉ ከዕሁዱ የማላዊ ጨዋታ በኋላ መጠነኛ ጉዳት በማስተናገዳቸዉ ምክንያት በትላንትናው ዕለት ብሐራዊ ቡድኑ በነበረዉ ልምምድ ላይ ቢገኙም ሙሉ ለሙሉ ልምምድ መስራት አለመቻላቸውን አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ገልጸዋል።
አሰልጣኙ አያይዘውም የሁለቱን ተጫዋቾች ጉዳት በተመለከተ በቀጣይ ቀናት በሚኖሩ ልምምዶች ላይ እንደሚገመገምም ተናግረዋል። ዋልያዎቹ የፊታችን ሀሙስ ምሽት 1ሰዓት ላይ ከፈርኦኖቹ ጋር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉም ይሆናል።