► መንግስት ለዋሊያዎቹ የቻን አፍሪካ ዝግጅትና ውድድር ተጨማሪ 15 ሚሊዮን ብር መፍቀዱ ተነገረ።
የፌዴሬሽኑ ዋናጸሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በተለይ ከሀትሪክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት “የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አህመድ ሽዴ የሰጠናችሁ 20.8 ሚሊዮን ብር እንደማይበቃ አውቀናል በማለት ተጨማራ 15 ሚሊዮን ለመስጠት መወሰናቸውን ገልጸዋል። ለዚህም በመላው ኢትዮጵያዊያን ስም እናመሰግናለን” ሲሉ ተናግረዋል።
“አንዳንዶች የቻን ውድድርን ለማኮሰስና ለማሳነስ ይፈልጋሉ ይሄ ቡድን ለቻን ሻምፒዮና ባያልፍ መቆሚያ መቀመጪያ የሚያሳጡን ወገኖች ቻን ከባድ ውድድር አይደለም እያሉ ነው ግን ለኛ ቻንም ናፍቆን እንደነበረ ይታወቃል 8 አመት ተነፋፍቀን እንደነበርም መታወስ አለበት” ያሉት ዋና ጸሃፊው ” አሁንም መንግስት ሁኔታውን አይቶ የገንዘብ ሚኒስትሩ የተከበሩ አህመድ ሽዴ የሰጠናችሁ ገንዘብ በቂ አይደለም ብለው 15 ሚሊዮን ብር ቃል በመግባታቸው ደስ ብሎናል ለዚህም እናመሰግናለን ክልሎችንም አግባብተንና አሳምነን ድጋፍ ሊያደርጉልን ቃል ገብተዋል ሲዳማ ክልል ፣ደቡብ ክልል፣ ሶማሌ ክልል፣ ደቡብ ምዕራብ ክልል፣ ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተውልናል በእኛም በኩል አንድ ኮሚቴ ተዋቅሮ ገንዘቡን የመሰብሰብ ስራ እየተሰራ ነው ኦሮሚያ ክልል፣አማራ ክልል፣ አዲስ አበባ ከተማና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችም ድጋፍ እንደሚያደርጉልን ቃል ገብተዋል ስፖንሰሮችንም አስተባብረን ጥሩ ድጋፍ ይገኛል ብለን እናምናለን” ሲሉ ተናግረዋል።
መንግስት ያደረገው ይኸው ድጋፍ ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ የሰጠውን ድጋፍ 35.8 ሚሊዮን ብር አድርሶታል።