በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ታሪክ ደቡብ ፖሊስን ሲዳማ ቡናን ሐዋሳ ከተማን አዳማ ከተማንና መከላከያን በዋና አሰልጣኝነት ደደቢትን ደግሞ የገብረ መድህን ሀይሌ ረዳት ሆኖ በማገልገል በሀላፊነት የሰራው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ሞውሪኖ የወላይታ ድቻ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።
ወላይታ ድቻዎች በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ጅማሬዎች ላይ የውጤት ማጣታቸውን ተከትሎ አሰልጣኛቸውን ደለለኝ ደቻሳን እና ረዳቱን ያሰናበቱ ሲሆን በቀጣይነት ቡድኑን የሚመራ አሰልጣኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲያፈላልጉ ከቆዩ በኋላም ነው ዘላለም ሽፈራውን እስከ ሰኔ 30 በሚደርስ ውል ሊቀጥሩት የቻሉት።
ወላይታ ድቻ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በማድረግ በ 3 ነጥብ በ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።