በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ደረጃ በመያዝ ወደታች የወረዱት ወልቂጤ ከተማዎች ጳውሎስ ጌታቸውን መቅጠራቸው ታውቋል።
በትግራይ ቡድኖች በቀጣይ ዓመት አለመሳተፍ ምክንያት ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የመመለስ አንድ እድል ያገኙት ክትፎቹ የመጨረሻውን የሊጉ 4 ጨዋታዎች ቡዱኑን ከመራው አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሐም ጋር ተለያይተዋል ።
በዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ አጋማሽ ላይ
ከጅማ አባጅፋር ጋር የተለያዩት አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ወልቂጤ ከተማን ተረክበዋል። በቀጣይ ለሚጠብቃቸው ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ ለሚደረገው ፍልሚያ የቡዱኑን ተጫዋቾች በመያዝ ወደ ሀዋሳ በማምራት ላይ ይገኛሉ።
ከሰኔ 18 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ዮንቨርሲቲ ስታዲየም ከከፍተኛ ሊጉ ሁለት ሁለተኛ የወጡት ሶስት ቡድኖች ከፕሪሚየር ሊጉ ከወረዱ ሶስት ቡድኖች ጋር ተፋለመው እሚያሸንፉ ሶስት ቡድኖች ለ2014ቱ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ እሚያድጉ ይሆናል ።