አሰልጣኝ ሙልጌታ ምህረትን ዋና አሰልጣኝ አድርገዉ በመሾም ለ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን አዳዲስ ተጫዋቾን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ የነባር ተጫዋቾችን ዉል እያደሱ ቅድመ ዝግጅታቸዉን በሀዋሳ ከተማ በመስራት ላይ የሚገኙት ሰራተኞቹ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርመዋል።
ወልቂጤ ከተማዎች ላለፉት ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቤት የተጫወተዉን ሙሉአለም መስፍንን በይፋ የክለባቸዉ 12ኛ ፈራሚ አድርገዉ ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።