ወልቂጤ ከተማን ባለፉት አመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ አበባው ሰለሞን ሃላፊነታቸውን በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ አስረክበዋል።
ፕሪሚየር ሊጉ ሲጠናቀቅ በይፋ በቃኝ ያሉት አቶ አበባው ዛሬ ጠዋት ወልቂጤ ከተማ ከንቲባው ቢሮ በመገኘት ሃላፊነታቸውን ለአዲሶቹ አመራሮች በይፋ አስረክበዋል።
አቶ አበባው ባለፉት አመታት በነበራቸው የአመራር ቆይታ ደስተኛ መሆናቸውና “በገባኝ ልክ በንጽህና ክለቡን በመምራቴ ኩራት ይሰማኛል” በማለት ከዓባይ ቲቪ የሜዳሊያ ፕሮግራም ላይ በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል።
የአቶ አበባው ሙሉ ቃለምምልስ ዛሬ ምሽት በዓባይ ቲቪ ላይ ይከታተሉ።