በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዉድድር ከ5ኛ ሳምንት በኋላ እንደሚቋረጥ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጥር 13 ጀምሮ ከታንዛኒያ ጋር ለሚያደርገዉ የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በቂ ዝግጅት ለማድረግ ይረዳው ዘንድም ዉድድሩ እንደሚቋረጥ የታወቀ ሲሆን ፤ ቀጣይ ዉድድሩ የሚጀምርበት ቀን እና የዉድድር ቦታዉ እንደሚገልፅም አወዳዳሪዉ አካል አስታውቋል።
የሴቶቹን ፕሪሚየር ሊግም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስት ጨዋታዎችን ተጫዉቶ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ላይ ተቀምጠዋል።