የ2015 ዓ.ም የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና የሴቶች ከፍተኛ ሊግ የዕጣ ማዉጣት ስነ-ስርዓት ከደቂቃዎች በፊት በጁፒተር ሆቴል ተከናውኗል።
አስቀድሞ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የሴቶች ልማትና ዉድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሂቢባ ሲራጅ የመክፈቻ ንግግር በጀመረዉ ጉባኤ ላይ የ2014 አመት አፈፃፀም ሪፖርት ፣ የዳኞች እና ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እና የ2015 አመት የዉድድር ደንብ ማብራሪያ ተሰጥቶበት ዉይይት ከተደረገበት በኋላ የዕጣ ማዉጣት ስነ-ስርዓቱ ተከናውኗል።
በዚህም መሰረት 13 ቡድኖች በሚሳተፉበት የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት ፕሮግራም:-
- ማሰታውቂያ -
አዲስአበባ ከተማ ከ አዳማ ከተማ
ንፋስ ስልክ ከ ይርጋጨፌ ቡና
ልደታ ክ/ከተማ ከ መቻል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ
ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ
ኤሌትሪክ ከ ቦሌ ክ/ከተማ
አራፊ ቡድን :- አርባምንጭ ከተማ
በተመሳሳይ በ14 ክለቦች መካከል የሚደረገዉ የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የአንደኛ ሳምንት ፕሮግራም:-
ሱሉልታ ከተማ ከ አራዳ ክ/ከተማ
ለሚኩራ ክ/ከተማ ከ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ
ሞጆ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ
በባህርዳር ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ
አቃቂ ቃሊቲ ከ ዎባአሪ ሻኪሚ
ሲዳማ ቡና ከ ሀምበሪቾ ከተማ
ቂርቆስ ክ/ከተማ ከ ፋሲል ከነማ
በተያያዘም ዉድድሮቹ ማለትም ከፍተኛ ሊግ በሰበታ ከተማ እንዲሁም ፕሪምየር ሊጉ በሀዋሳ ከተማ ከህዳር 10 ጀምረዉ መከናወን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።