በሁለት ምድብ ተከፍሎ በዘጠኝ ክለቦች መካከል ሲደረግ የቆየዉ የሴቶች የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና በአንቦ ጎፋ አሸናፊነት በዛሬዉ እለት ተጠናቋል።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከሰኔ 15 ጀምሮ በ2 ምድቦች ተከፍሎ በ9 ክለቦች መካከል በሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት ሲደረግ የቆየዉ የ2015 አ/ም የሴቶች የክልል ክለቦች ሻምፒዮና በዛሬው እለት በተደረጉ ሁለት መርሀ ግብሮች ፍፃሜዉን አግኝቷል።
- ማሰታውቂያ -
በማስቀደም 7:00 ሰአት ሲል ለደረጃ ጨዋታ ሲዳማ ፓይለት እና ጉለሌ ክ/ከተማ ተገናኝተዉ ጨዋታዉን ሲዳማ ፓይለት 2-1 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ዉድድሩን በሶስተኝነት በማጠናቀቅ የነሀስ ሜዳልያ ተሸላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
በማስከተል 9:00 ሰአት ጀምሮ የፍፃሜዉ የዋንጫ ጨዋታ በአምቦ ጎል ፕሮጀክት እና በደብረማርቆስ ከተማ መሀከል የተደረገ ሲሆን ጨዋታዉን አምቦ ጎል ፕሮጀክት 5-1 በሆነ ዉጤት አሸንፎ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።
አቶ አዲሱ ቃሚሶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፣ አቶ አንበሴ አበበ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ አቶ ፍሮምሳ ለገሰ የኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ሌሎችም በክብር እንግድነት በመገኘት ጨዋታዎቹን ያስጀመሩ ሲሆን ለአሸናፊ ቡድኖችም ሽልማትን አበርክተዋል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት ቀጥሎ ሲደረግ አምቦ ጎል ፕሮጀክት የወርቅ ሜዳሊያ፣ የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ እና የሻምፒዮንነትን ዋንጫ ከእለቱ የክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዋል። ደብረ ማርቆስ ከተማ የብር ሲዳማ ፓይለት ፕሮጀክት ደግሞ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
ወደ 2016 ዓ/ም የዉድድር ዘመን ወደ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ አምቦ ጎል ፕሮጀክት እና ደብረማርቆስ ከተማ አድገዋል።