ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ ሲተላለፉ በተጫዋች የሲዳማ ቡናዉ የመስመር ተጫዋቾች ይገዙ በጋለ ቅጣት ተጥሎበታል።
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ጥ በ6ተኛ ሳምንት በተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
#በተጫዋቾች_ደረጃ:- ግርማ በቀለ የተጋጣሚን ቡድን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሲሆን 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት 3ሺ ብር እንዲከፍል ፣ ቢኒያም ገነቱ እና መድሃኔ ብርሀኔ ቀይ ካርድ በመመልከታቸው ምክንያት አንድ ጨዋታ እንዲታገዱ እንዲሁም ይገዙ ቦጋለ በሳምንቱ ጨዋታ ጎል ካስቆጠረ በኋላ የማዕዘን ባንዲራ ስለመስበሩ ሪፖርት ስለተደረገበት ባጠፋው ጥፋትም 10, 000 ብር እንዲከፍል እና የተሰበረውን ንብረት እንዲተካ ወይም አወዳዳሪው አካል የሚያቀርበውን የንብረትን ዋጋ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡
- ማሰታውቂያ -
#በክለቦች ደረጃ:- ሃዋሳ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ፣ ወላይታ ድቻ እና ሀዲያ ሆሳዕና በሳምንቱ ጨዋታቸው የክለባቸው አምስትና ከአምስት በላይ ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ ምክንያት 5,000 ሺ ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡