የዛምቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሚሉቲን ሰርጆቪች (ሚቾ) ጋር በጋራ ስምምነት መለያየቱ ይፋ ሆኖአል፡፡ የፌደሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አድሪያን ካሻላ በሰጡት መግለጫ ሁለቱም ወገኖች ተገናኝተው መስማማታቸውን ገልፀዋል።
እግርኳስ ፌደሬሽኑ ከዋናው የወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሚሊቲን ሚቾ ስሬዶጄቪች ጋር ለመለያየት ስምምነት ላይ መድረሱን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የኤፍኤዝ ዋና ፀሃፊ አድሪያን ካሻላ በፌደሬሽኑ እና በአሰልጣኙ መካከል ድርድር ከተደረገ በኋላ ለሁለቱም ወገኖች እድገት እና መሻሻል እንዲኖር ሲባል ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል ፡፡
በተጨማሪም እግርኳስ ፌደሬሽኑ እስከ የካቲት 3 ቀን 2020 ዓ.ም ድረስ ብሔራዊ ቡድኑን በመምራታቸው አሰልጣኝ ሚቾን አመስግነዋል፤ በሚቀጥለው የስራ ሂወታቸዉም መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል ፡፡
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኝ ሚቾም በቆይታቸው ለፌዴሬሽኑ እና ለዛምቢያ ህዝቦችም ስላደረጉላቸው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
”በዛምቢያ ህዝብ ፣ በተጫዋቾች ፣ በአሰልጣኞች ፣ በባለስልጣናት እና በቆይታዬ በተለያዩ መንገዶች የደገፉኝ አድናቂዎቼን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ ዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያሉኝ ሁሉም አዎንታዊ ልምዶች ወደፊት በሙያዬ ውስጥ እጠቀማለሁ፤ እናም ለዛምቢያ መልካም ነገሮችን ሁሉ መመኘት እፈልጋለሁ ”ብለዋል የቀድሞው የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ሚሉቲን ሰርጆቪች (ሚቾ)፡፡