ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣን ያንብቧት፤ ይደሰቱባታል
ሀትሪክ ስፖርት ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃ ተወዳጅ ጋዜጣ ናት፤ በባለቀለም ከለር አሸብርቃ በሳምንት አንድ ቀን ገበያ ላይ የምትውለው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማለዳም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን በሚወዱት መልኩ ይዛሎት በመቅረብ እናንተን ምርጥ አንባቢዎች ልታገኝ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ለመሆኑ ነገ ገበያ ላይ ስትውል ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ዘገባዋ የብዙዎቹን ትኩረት እየሳበ እና ተወዳጅነትንም እያተረፈ በመጣው ARJSEN ROBBEN ዓምዷ የእዚህ ሳምንት እንግዳ አድርጋ ያቀረበችው ተጨዋች በፕሪምየር ሊጉ በአሁን ሰዓት ለመከላከያ ክለብ እየተጫወተ የሚገኘውን የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የመከላከያ፣ የደደቢት፣ የኢትዮጵያ ቡና፣ የድሬዳዋ ከነማ፣ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ የፋሲል ከነማ እና እንደዚሁም ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች የነበረውን ዳዊት እስጢፋኖስን ሲሆን ከተጨዋቹ ጋር በእግር ኳሱ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ በራሱ ተጨዋችነት ዙሪያና ከቤተሰቡ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተንለት ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ ሌላ ይዛሎት የቀረበችው ዘገባ የቅ/ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ እሁድ ዕለት በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት ስላካሄደውም የጠቅላላ ጉባኤው ሰፋ ባለ መልኩ ዘገባን የሰራን ሲሆን፤ ሌሎችም ስፖርታዊ መረጃዎችን በነገው እትም እናስነብቦታለን፤ ሀትሪክ አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ነገ የምታስነብቦት ምርጥ ምርጥ ዘገባ ያላት ሲሆን ከእነዚህ መካከልም፤ ማክሰኞ እና ረቡዕ በሚካሄዱት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ዙሪያም፤ ከሚካሄዱት ተጠባቂ ግጥሚያዎች መካከል በአትሌቲኮ ማድሪድ እና በጁቬንቱስ እንደዚሁም ደግሞ በሊቨርፑል እና በባየርን ሙኒክ ጨዋታ ዙሪያ ጥልቅ መረጃን አቅርበንሎታል፤ ሀትሪክን አንብቧት፤ የእናንተው ናት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡