ሀትሪክ ስፖርትን ነገ ይጠብቋት ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሳምንታዊዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም በተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎች ታጅባ ለእናንተ ውድና የተከበራችሁ አንባቢዎች በእጃችሁ ትደርሳለች፤ ሀትሪክ ስፖርት በሀገር ውስጥ የነገው እትሟ ይዛላችሁ ከምትቀርበው ዘገባ ውስጥ በተጠባቂውና በአቻ ውጤት ስለተጠናቀቀው የቅዱስ ጊዮርጊስና የደደቢት ጨዋታ እና የሁለቱ ክለብ ረዳት አሰልጣኞች ፋሲል ተካልኝና ጌቱ ተሾመ ከጨዋታው በኋላ ስለሰጡት አስተያየት የምናስነብባችሁ ሲሆን ከእዚያ ውጪ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሐዋሳ ከተማ ሀሙስ በሚያደርጉት ጨዋታ ዙሪያም የሐዋሳ ከተማው አሰልጣኝ ውበቱ አባተም የሰጠው አስተያየት ይጠቀሳል፤ ሌላው ሀትሪክ ከምታስነብባችሁ ውስጥ የጋቶች ፓኖም ዝውውርን አስመልክቶ በእሱ መንገድ ላይ ፊፋና አንዚ ማካቻካላ ስለቆሙበት ሁኔታም ዘገባም ቀርቧል፤ ሀትሪክ ነገ እንዳታመልጦት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ሌላ ዘገባ ውስጥ የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ላይ በነገው ጋዜጣችን እንግዳ አድርገን ያቀረብነው በተጨዋችነት ዘመኑ ለኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣትና ለዋናው ብሔራዊ ቡድን፣ ለኤሌክትሪክ፣ ለሰሚት ለኒያላና ለአየር መንገድ ተጫውቶ ያሳለፈውን ያሬድ ከበደን ሲሆን ተጨዋቹ ከሰጠው አስተያየት ውስጥ በተጨዋችነት ዘመኑ የቋሚ ተሰላፊ ተጨዋች ሆኖ የእግር ኳስ ዘመኑን በማጠናቀቁ በጣም ደስተኛ ስለመሆኑ ይናገራል፤ ከእዚያ ውጪም የቀድሞ የክለብ አጋሩ ሲሳይ ተሰማ በመሀል ተከላካይነት ሁሌ ቢጫወት ማንም ሌላ ተጨዋች በቦታው አይታወቅምም ነበር ይላል፤ በኳስ ህይወቱ ዙሪያ ያሬድ ከእኛ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታን አድርጓል፤
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿ ደግሞ ነገ የምታስነብባችሁ ከእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ከነበሩት ግጥሚዎች መካከል ማንቸስተር ዩናይትድ በቼልሲ ላይ ስለተቀዳጀው ድል አስመልክቶ ዘገባ ይዘንላችሁ የቀረብን ሲሆን በካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታም ማንቸስተር ሲቲ አርሰናልን በሰፊ ግብ አሸንፎ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ዋንጫ በማንሳቱ ዙሪያ መረጃን ልናቀርብላችሁ ችለናል፤ በሌሎች የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች፤ የስፔን ላሊጋና የሌሎች ሊጎችንም አስመልክተን ከመዝናኛ አምዶቻችን ጋር ለእናንተ ሰፋ ያሉ መረጃዎችን አቅርበናል፡፡
በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት ስለተካሄዱ የውስጥ ውድድሮችም መረጃዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ ሀትሪክ የእናንተ ናት ይወዷታል፤ ያንብቧት
ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፡፡
- ማሰታውቂያ -
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ