የአስራ ሁለተኛው ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር በዚህ ሳምንትም ሲካሄዱ ለተመልካች አዝናኝ በሆነ መልኩ ብዙ ጎሎች የተቆጠሩበት ሳምንት ሆኖ አልፏል ፡፡ ሊጉ ከረጅም ቆይታ በኋላ ፈረሰኞቹን በአንደኛ ደረጃ ላይ አቆናጧቸዋል፡፡
ፈረሰኞቹ ሊጉን በተመሳሰይ በባለፈው የውድድር ዓመት ጥር 17 2011 ዓ.ም ሊጉን መምራት ሲችሉ በመሪነት መቆየት የቻሉት ግን እስከ የካቲት ሶስት ብቻ መሆን ሲታወስ በሳምንቱ መጨረሸ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከ 381 ቀናት በኋላ ዳግም ወደ መሪነት ለመመለስ ችለዋል ፡፡
ሀትሪክ በሳምንቱ ከነበሩ የሊጉ መርሀ ግብሮች ክሰተቶችን እና መረጃዎችን ለእናንተ ቤተሰቦቻችን ያደርሳል!
- ማሰታውቂያ -
ፕርሚየር ሊጉ ከአምናው የውድድር ዓመት በተለየ መልኩ እየተካሄደ ቢቆይም ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ ግን ተቃውሞዎችን ማሰማቱን ሲጀምር ደጋፊዎችም የጉዳት ሰለባ መሆናቸው በአንድ አንድ ስታዲየሞች ላይ ታይተዋል ፡፡
ለአብነትም በአዳማ ያለፉትን ሁለት ሳምንታት የሀድያ ሆሳዕና ፤ ጅማ አባ ጅፋር እና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ጉዳት ደርሶባቸው ታይቷል ፡፡ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡና ፤ ፋሲል ከነማ እና ጅማ አባ ጅፋር ደጋፊዎች በክለቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞንም ሲያሰሙ ተሰምተዋል ፡፡
ምንም እንኳ ሊጉ በዚህ ሳምንት ይህንን ክሰተቶች ቢያሳይም ከአስራ አንዱ ሳምንታት የተሻለ የጎል ብዛት ሀያ አራት ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሜዳው እና በደጋፊዎቹ ፊት ሲዳማን ያሸነፈበት ጨዋታ ስምንት ጎሎችን በማስተናገድ ቀዳሚው ነው ፡፡
የአስራ ሁለቱ ሳምንታት ጉዞ ከ 2011 የውድድር ዓመት ጋር ሲነፃፀር !
በአስራ ሁለት ሳምንታት የዘንድሮው ጉዞው ከአምናው የውድድር ዓመት ጋር ሲነፃፀር በነጥብ ረገድ አንሶ ይገኛል ፡፡ ፈረሰኞቹ ከአምናው ካስመዘገቡት 24 ነጥቦች በአንድ አንሰው ሲገኙ በጎል ክፍያውም ቢሆን በአምስት ጎሎች ያንሳሉ፡፡
ኢትዮጵያ ቡና በዚህን ወቅት ከሁሉም ቡድኖች በልጠው 13 ጨዋታዎችን ሲያደርጉ 22 ነጥቦችን ሲሰበስበቡ አሁን ላይ ካስመዘገቡት በ 11 ነጥቦች አንሶ ይገኛል ፡፡
የአምናው ሻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ አስር ጨዋታዎችን ሲያደርጉ ሻምፒዮን ከሆኑበት ዓመት ( 26 ነጥቦች ) ያነሰ በዘንድሮው የአስራ ሁለት ሳምንታት ጉዞው ( 22 ነጥቦችን ) ማስመዝገብ ችለዋል ፡፡
በአጠቃላይ እንደ ትልቅ ለውጥ ከሚታዩ ክለቦች አንዱ ስሑል ሽረ ሲሆን አምና ካስመዘገቡት ነጥቦች አንፃር በስምንት ነጥቦች ከፍ ብለው በደረጃው አናት ላይ ተጠግተው ተቀምጠዋል ፡፡
የወላይታ ዲቻው እዮብ አለማየሁ እስከ ስምንተኛው ሳምንት ድረስ በአዲስ ግደይ ተይዞ የቆየውን የሊጉ ፈጣን ጎል አግቢነት ድሬድዋን በታሪካቸው ለመከመሪያ ጊዜ ባሸነፉበት ጨዋታ በአርባኛው ሴኮንድ ላይ ያስቆጠራት ግብ በሊጉ አዲስ ታሪክ እንዲፅፍ አድርጎታል ፡፡
በአስራ ሁለተኛው ሳምንት መርሀ ግብሮች ላይ በሜዳቸው የተጫወቱ ሁሉም ቡድኖች ድል ሊቀናቸው ሲችል ሀያ አራት ጎሎች ከመረብ ላይ አርፈዋል ፡፡
ይህም በአጠቃላይ የሊጉ ጉዞ ላይ ከፍተኛው ብዙ ጎሎች ከተስተናገዱበት ሳምንታት አንዱ ለመሆን ችሏል ፡፡
ከተቆጠሩት ሀያ አራት ጎሎች መካከል አቤል ያለው ፤ ጌታነህ ከበደ ፤ እዮብ አለማየሁ እና አህመድ ሁሴን ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ቀዳሚዎቹ ተጫዋቾች ናቸው ፡፡
እንዲሁም ደግሞ አራት ጎሎች በውጭ ሀገር ተጫዋቾች ሲቆጠሩ የስሑል ሽረ ተጫዋቾች ሳሊፍ ፎፎና እና አብድልለጢፍ መሀመድ ቀዳሚዎቹ ተጫዋቾች ናቸው ፡፡
በሳምንቱ ከመረብ ላይ ካረፉት 24 ጎሎች ውስጥ ግሩም አሰፋ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ግብ በብቸኝነት ሲቆጠር የሙጂብ ቃሲም እና አዲስ ግደይ ብቸኞቹ የፍፁም ቅጣት ምት አስቆጣሪዎች ናቸው ፡፡
በሊጉ የአስራ ሁለት ሳምንታት ጉዞ 220 ጎሎች ከመረብ ላይ ማረፍ ሲችሉ የኢትዮጵያ ቡናው ሀብታሙ ታደሰ 100ኛውን ፤ የወልዋሎ አዲግራት ዩ. አጥቂ ኢታሙና ኬሙዬኔ 150ኛውን እንዲሁም በሳምንቱ መጨረሻ የአዳማ ከተማው ዳዋ ሆቴሳ 200ኛዋን ጎል ማስቆጠር ችለዋል ፡፡
ሙጂብ ቃሲም በአስር ጎሎች የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሲመራ ይህም ከባለፈው የውድድር ዓመት የወቅቱ ኮከብ ግብ አግቢዎች አዲስ ግደይ እና ዳዋ ሆቴሳ በሁለት ግቦች ከፍ ብሎ ይገኛል ፡፡