በክረምቱ የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ሀድያ ሆሳእናን የተቀላቀለው አንጋፋው አጥቂ መሐመድ ናስር ከሀድያ ሆሳእና ጋር በስምምነት ተለያይቷል።
በጉዳት ምክንያት አዲስ አዳጊውን ሀድያ ሆሳእናን እንደተጠበቀው ማገልገል ያልቻለው የቀድሞው የኒያላ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ኢትዮጵያ መድን፣መከላከያ፣አዳማ ከተማ፣ኢትዮጵያ ቡና፣ጅማ አባቡና፣ፋሲል ከነማ፣ሲዳማ ቡና እና የሱዳኑ አልአህሊ ተጨዋች ከክለቡ ጋር ሚያቆየው የአንድ ዓመት ውል ቢኖረውም ከክለቡ በጋራ ስምምነት መለያየት ችሏል።
ከመሐመድ ናስር ጋር የተለያዩት ሀድያዎች የካቲት 16 ይከፈታል ተብሎ በሚጠበቀው የግማሽ ዓመት የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ላይ የአጥቂ ክፍላቸውን ለማጠናከር ገበያው ላይ በንቃት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።