ሃዲያ ሆሳዕና ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በነበረው ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ጨዋታው መጠናቀቁን
ተከትሎ ባስነሱት ረብሻ የመቐለ ወጌሻ መፈንከቱን ከጨዋታ አመራሮች ሪፖርት የቀረበለት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሃዲያ ሆሳዕና ቀጣይ 5 የሜዳውን ጨዋታ ከሜዳ ውጪ እንዲጫወትና 110ሺ ብር እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
የጨዋታ ሜዳዎቹን አወዳዳሪው አካል እንዲመርጥ ውሳኔው በወጣ በ7 ቀን ውስጥ የቅጣት ገንዘቡን እንዲከፍሉ የማይከፍሉ ከሆነ በየቀኑ የቅጣቱ ወለድ 2% በመቶ እንደሚጨምር ተወስኗል፡፡ ውሳኔውን የማያከብሩ ከሆነ ከፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ምንም አይነት ግልጋሎት እንዳያገኙ መወሰኑ ታውቋል፡፡