ከ60 ሺህ በላይ ደጋፊ በትግራይ ስታድየም ታድሞ በተከታተለው የመቐለ 70 እንደርታ ና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ በባለ ሜዳዎቹ ምዓም እንበሳዎች እሸናፊነት ተጠናቋል።
ብዙ ሙከራዎች እና የመቐለ 70 እንደርታ የኳስ ቁጥጥር ና ሙከራ በላይነት በታየበት የመጀመርያው ጥሩ ሚባል ፋክክር አሳይቷል።በ4-2-3-1 የተጨዋቾች እሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት መቐለዎች ከሁለቱም መስመሮች በሚነሱ ኳሶች እድሎችን ሲፈጥሩ ነበር፤በተለይም ኦሰይ ማውሊ፣ያሬድ ብርሃነ ና እማኑኤል ገብረሚካኤል ያደረግዋቸው ሙከራዎች ሚጠቀሱ ናቸው።እንግዶቹ ድሬዎች እብዛኛው ጊዚያቸውን መሃል ሜዳ ላይ ትኩረት ያደረጉ እጫጭር ና የተቆራረጡ ቅብብሎሽ ከማድረግ ውጪ ይህ ሚባል የግብ ዕድል መፍጠር ተስንዋቸው ታይቷል።መደበኛ የመጀመርያ እጋማሽ ተጠናቆ ዳኛው በጨመሩት 3 የባከኑ ደቂቃዎች ላይ እማኑኤል መትቶት በድሬዳዋ ተከላካዮች በእጅ መመለሱ ተከትሎ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ጋናዊው ኦሰይ ማውሊ እስቆጥሮ የመጀመርያው እጋማሽ በመቐለ መሪነት እንዲጠናቀቅ እድርጓል።
- ማሰታውቂያ -
ሁለተኛው እጋማሽ መቐለዎች ያሬድ ብርሃነን በዮናስ ገረመው በመቀየር የጨዋታ ስልታቸውን ወደ 4-4-2 በመቀየር ተጫውተዋል።ድሬዎች በበኩላቸው መጀመርያ እጋማሽ ላይ የተጠቀሙበት እሰላለፍ ለውጥ ሳያደርጉ ገብተዋል።ጫና መፍጠራቸውን የቀጠሉት መቐለዎች 55ኛው ደቂቃ ላይ ዮናስ ገረመው ከማእዘን ምት ያሻገረውን ኳስ የድሬ ተከላካዮች ኳሱን በሚያወጡበት ጊዜ በእጅ መንካታቸውን ተከትሎ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት እማኑኤል ገብረሚካኤል እስቆጥሮ የመቐለን ጎል ወደ ሁለት ከፍ ማድረግ ችሏል።
ከግቡ መቆጠር በኃላ በተሻለ መልኩ ሙከራዎችን ማድረግ የቻሉት ድሬዎች ከርቀት በሚመቱ ኳሶች እድሎችን መፍጠር ችለዋል፤የዚህም ውጤት በ78ኛው ደቂቃ ላይ ኤልያስ ማሞ የበረኛው ሶፈንያስ ሰይፈ መውጣትን ተምልክቶ ከርቀት የመታው ኳስ ቀጥታ የመቐለ መረብ ላይ ሊያሳርፈው ችሏል።ከግቡ በኃላ መቐለዎች መሪነታቸውን ለማስጠበቅ ያደረጉት ሙከራ ተሳክቶላቸው ጨዋታው 2ለ1 ማሸነፍ ችለዋል።
ሽረ ላይ የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ መቐለ 70 እንደርታ የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ሊሆን ችሏል።