በ1999 የተመሰረተው መቐለ ከተማ ባለፋት ሁለት ዓመታት በደጋፊው ሲነሳ የነበረውን የስም መቀየር ጥያቄ በመቀበሉ ካሁን በኃላ የክለቡ መጠርያ ‘መቐለ 70 እንደርታ’ መሆኑን ኣስታውቋል።የህዝቡ ፍላጎት ለማወቅ በማህበራዊ ድህረ ገፆችና በሌሎች መንገዶች ምርጫ ሲያካሂድ የነበረው ክለቡ በመጨረሻም የክለቡ ስም ኣብዛኛው ደጋፊ የመረጠውን ስም እንዲሆን፤በተጨማሪም የክለቡ ቅጥያ ስም ‘ምዓም ኣንበሳ’ እንዲሆን ተወስኗል።
የክለቡ ኣርማ (Logo) በተመለከተም በቅርብ ቀን ደጋፊ የመረጠውን ንድፍ ተመርኩዞ ኣዲስ ኣርማ ተዘጋጅቶ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።