ማሊያዊ ሲዲ ኬታ በፈረሰኞቹ ቤት የሚጠበቀውን ያህል ግልጋሎት ባለመስጠቱ ከ4 ወራት ቆይታ በሇላ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡
ፈረሰኞቹ ከዩጋንዳው ኬሲሲኤ ጋር ለነበራቸው የካፍ ቻምፒዬንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ካምፓላ ሲያቀኑ ከጨዋታው መልስ ክለቡ ተጨዋቾችን ሊያሰናብት እንደሚችል መነገሩ የሚታወስ ሲሆን ከክለቡ ጋር በስምምነት የተለያየው የመጀመሪያው ተጨዋች ኬታ ቢሆንም ከክለቡ ጋር ሊለያዩ የሚችሉ ተጨዋቾች ስለመኖራቸው ክለቡ በይፋ ባያሳውቅም እየተነገረ ነው፡፡
ፈረሰኞቹ ተጨዋቹን በ2 ዓመት ኮንትራት ውል ጥቅምት 2010ዓ/ም ሲያስፈርሙት በኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ውድድር ባለፈም ኢትዮጵያን በመወከል በሚሳተፉበት የአፍሪካ መድረክ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ነበር፡፡ነገር ግን ፈረሰኞቹ ዘንድሮ በአፍሪካ ቻምፒዬንስ ሊግ ያሰቡትን ያህል ሳይጓዙ በዩጋንዳው ኬሲሲኤ በጊዜ ተሸንፈው ሲወጡ በፕሪሚየር ሊጉም ቢሆን ውጤታማ ናቸው ለማለት እስካሁን ያስመዘገቡት ውጤት አያስደፍርም፡፡
ተጨዋቹ ከክለቡ ጋር በነበረው የአጭር ጊዜ ቆይታም ቢሆን ተቀይሮ በተጫዎተባቸው የሊግ ጨዋታዎች ክለቡ ከሱ የሚፈልገውን ግልጋሎት መስጠት ባለመቻሉ የነበራቸውን የ2 ዓመት ኮንትራት ውል በስምምነት በማቋረጥ መለያዬታቸውን ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ የገለፀ ሲሆን ተጨዋቹ ስለነበረው ቆይታ በማመስገን በሄደበት መልካም ነገር እንዲገጥመው ተመኝተዋል ፡፡
- ማሰታውቂያ -
Photo credit-st George official page