አዲስ ቡድን ግንባታ ላይ ሚገኙት ድሬዎች የአጥቂ ክፍላቸውን ለማጠናከር ሪችሞንድ አዶንግን አስፈርመዋል።
በ2010 አጋማሽ የዛምቢያውን ቢዩልድኮንን በመልቀቅ ቢጫ ለባሾቹን የተቀላቀለው ኦዶንጎ ከአንድ ዓመት ግምሽ ቆይታ በኃላ ከወልዋሎ ጋር ተለያይቷል።የቀድሞው የቤሬኩም ቸልሲ(ጋና)፣ቢዩልድ ኮን(ዛምቢያ)፣ሳሀም ክለብ(ኦማን)፣አሚዳውስ ፕሮፌሺናልስ(ጋና)፣ሊበርቲ ፕሮሼሽናልስ(ጋና) ተጨዋች ሪችሞንድ አዶንግ ወሳኝ የአጥቂ ተጨዋቾቹን ሀብታሙ ወልዴ ና ኢታሙና ኩሜይኒ ያጣውን የድሬ አጥቂ ክፍልን ሚመራ ይሆናል።
በተጫማሪ ዘካርያስ ቱጂ ና ፋሲል አስማማውን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሶ የነበረው ድሬዳዋ ከተማ በመጨረሻ ሰዓት ዝውውሮቹ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳኩ ቀርተዋል።