በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 4ኛ ሳምንት ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ና ወላይታ ድቻ ተገናኝተው ባለሜዳው ሀዋሳ ከተማ ያቡን ዊልያም ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ሀይል የተቀላቀለበት እና የመሀል ሜዳ ሽኩቻ የተስተዋለበት ይህ ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ይሄ ነው የሚባል እንቅስቃሴ አልተስተዋለበትም። አልፎ አልፎ የሀዋሳ ከተማው ፍሬው ሰለሞን(ጣቁሩ) ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል የሚጥላቸው ኳሶች አደገኛ ነበሩ።
በ35ኛው ደቂቃ ላይ ከመሀል ሜዳ ፍሬው ሰለምን የሰነጠቀለትን ኳስ ዳዊት ፍቃዱ (አቡቲ) ቺፕ በማድረግ የሞከራት ኳስ የግቡን አግዳሚ ታካ ልትወጣ ችላለች። 40ኛው ደቂቃ ላይ የሀዋሳ ከተማው አዲስዓለም ተስፋዬ ወደ ጎል ያሻማትን ኳስ ፍሬው ሰለሞን ጣቁሩ ሳይጠቀምባት ቀርታለች፡፡
ከመጀመሪያው አጋማሽ ይልቅ በጋለ ስሜት የተጀመረው ሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያውን ሙከራ ለማሳየት 9ደቂቃዎች ወስዷል።
- ማሰታውቂያ -
54ኛው ደቂቃ ላይ ታፈሰ ሰለሞን ያሻገረለትን ኳስ ዳዊት ፍቃዱ ሲመታው የወላይታ ድቻው ግብ ጠባቂ ኢማኑኤል ፌቮ አድኗታል።
በ74ኛ ደቂቃ ላይ ሀይማኖት ወርቁን በሁለት ቢጫ ያጣው ወላይታ ድቻ ቀሪውን 16 ደቂቃዎች በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት ተገደዋል፡፡
ሀዋሳ ከተማ መሀል ሜዳ ላይ ተጭነው በመጫወት እና ወደ ጎል በመድረስ ጥሩ እሚባሉ ነበሩ፡፡ በ84 ደቂቃ ላይ ታፈሰ ሰለሞን ከ16.50 ውጪ በእለቱ ጥሩ ለነበረው ፍሬው ሰለሞን ያሳፈለትን ኳስ ፍሬው በጭንቅላት ማይነስ ያደረገለትን ኳስ ያቡን ዊሊያም በግሩም ሁኔታ ከመረብ አዋህዷታል፡፡
ከጎልዋ መቆጠር በኃላ በተለምዶ የካታንካ ቦታ የሁለቱ ክለብ በደጋፊዎች የተነሳ ረብሻ ጨዎታው ለ18 ደቂቃዎች ለመቋረጥ ተገዷል በረብሻውም የተወሰኑ ደጋፊዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች የተቆጠረው ጎል ከጨዋታ ውጪ ነው በሚል የክስ ሪዘርቨ ማስያዝ ችልዋል፡፡ ጨዋታም 1-0 በሆነ ውጤት ሀዋሳ ከተማ ማሸነፍ ችሏል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ውበተ አባቱ-ሀዋሳ ከተማ
-ከእረፍት በፊት ጥሩ አልነበርንም ከእረፍት መልስ እንደ ባለሜዳ ተጭነን ተጫውተን ጎል አስቆጥረን መውጣት ችለናል፡፡
-በመከላከል ላይ የነበረን፡ባላንስ መልካም እሚባል ነው፡፡ ጎል እንዳይቆጠርብን ረድቶናል
ሁለት ቡድኖች ናቸው እሚጫወተው እሚያሸነፈው ግን አንዱ ነው፡፡ሁለቱ ቡድኖች ወንድማማቾች ናቸው፡፡ ስፖርታዊ ጨዋነት በስታዲየሞቻችን ሊሰርፅ ይገባል፡፡
መሳይ ተፈሪ -ወላይታ ድቻ
ሀዋሳ ከተማ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ግዜ ጥሩ ነበሩ፡፡ ሆኖም በሁለተኛው አጋማሽ ከጨዋታው ውጪ በሆነ ጎል አሸንፈውናል፡፡
-ዳኛው ለሐይማኖት ወርቁ የተሰጠው ካርድ ቅሬታ የለኝም፡፡ ከጨዋታው ውጪ የገባብን ኳስ ላይ ብቻ ነው ዳኛው ላይ ቅሬታ ያሳደረብን፡፡
-የግድ ማሸነፍ አለብን ብይ አላምንም በስራ ነው እምናምነው፡፡ በምንም ምክኒያት ድንጋይ መወራወር የለበትም ስፖርታዊ ጨዋነት አስፈላጊ ነው፡፡