ባህርዳር ከተማ ና መቐለ 70 እንደርታ ያገናኘው የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በባህርዳር ከተማ ኣሸናፊነት ተጠናቋል።ባለሜዳዎቹ ባህርዳሮች ባሳለፍነው ሳምንት ሃዋሳ ላይ እንድ ነጥብ ይዞ ከመጣው ስብስብ ማራኪ ወርቁ፣ወንድሜነህ ደረጃ ና ግርማ ዲሳሳን በኣቤል ውዱ፣ወሰኑ ዓሊ ና ሳላእምላክ ተገኝ ሲቀይሩ መቐለዎች በበኩላቸው ወላይታ ድቻ ላይ ድል ካስመዘገበው ቡድን ያሬድ ብርሃነን በኦሰይ ማውሊ ቀይረዋል። ተመጣጣኝ ፋክክር እና ብዙ ሙከራዎች በታዩበት የመጀመርያ እጋማሽ ባህርዳር ከሁለቱም መስመር በሚነሱ ኳሶች መቐለዎች በበኩላቸው ሁለት የፊት እጥቂዎቹን እማኑኤል ገብረሚካኤል እና ኦሰይ ማውሊ ኢላማ ባደረጉ ረጃጅም ኳሶች የግብ እድሎችን ለመፍጠር ችለዋል።
የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራ ወሰኑ ዓሊ በፍጹም ቅጣት ሳጥን ውስጥ በቀኝ መስመር በኩል ያገኛውን ኳስ ወደ ግራ በማጠፍ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ከግቡ ጎን ለትንሽ ወጥቷል።መቐለዎችም የመጀመርያ ሙከራቸውን ከማእዘን ምት ሚኪኤለ ደስታ ያሻማው ኳስ ያሬድ ከበደ በግምባሩ ቢገጨውም ሃሪሰን ሄሱ እድኖበታል።በ4-4-2 የጨዋታ ስልት እራቱ እማካዮቻቸውን ወደ ኃላ በመመለስ መጫወትን የመረጡት መቐለ እማኑኤል ገብረሚካኤል እና ኦሰይ ማውሊ ሁለቱም ወደ ጎን በመለጠጥ ከመስመር በመነሳት የባህርዳር ተከላካይ ክፍልን ለመረበሽ ሞክረዋል።የዚህም ማሳያ እማኑኤል በግራ መስመር በረጅሙ ያገኝውን ኳስ በፍጥነት ተጨዋቾችን በመቀነስ ያሻገረው ኳስ ኦሰይ ማውሊ ቢመታውም አሁንም ሃሪሰን እድኖበታል።
- ማሰታውቂያ -
መሃል ላይ ብልጫ የወሰዱት የጣና ሞገዶቹ ከመሃል ወደ ሁለቱም መስመር ለዜናዊ ፈረደና ወሰኑ ዓሊ በሚደርሱ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ያደርጉዋቸው ሙከራዎች በመቐለ ተከላካይ ክፍል ሲመለስባቸው ነበር።በረጃጅም ኳሶች እድሎች መፍጠራቸውን የቀጠሉት መቐለ ከመሃል ሜዳ ያሬድ ከበደ የላከውን ኳስ ኦሰይ ማውሊ የባህርዳር ተከላካዮችን በማለፍባህርዳሮች ቢሞክረውም ከግቡ እናት ወጥቷል።መስመር ላይ ትኩረት ያረገው የባህርዳር አጨዋወት በ19ኛው ደቂቃ ፍሬ ማፍራት ችሏል ከቀኝ መስመር ሳላእምላክ ተገኝ የመታው ኳስ የበረኛው ፊሊፕ ኦቮኖ መዘናጋት ታክሎበት የመቐለ መረብ ላይ እርፏል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ተጨማሪ ግብ ለማግኘት በዜናው ፈረደ እና ወሰኑ ዓሊ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ሁለተኛ ግብ ሳያስቆጥሩ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
ሁለተኛው እጋማሽ ላይ ዮናስ ገረመውን በሚኪኤለ ደስታ በመቀየር የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰዱት መቐለ ብዙ የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል።በተለይም ያሬድ ከበደ በግራ መስመር ከዮናስ ገረመው ያገኘውን ኳስ ወደ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ይዞ በመግባት ቢሞክረውም የጨዋታው ኮከብ ሃሪሰን ሄሱ እድኖበታል በተጨማሪም ጨዋታው ማገባደጃ ላይ ሃይደር ሸረፋ መሃል ለመሃል ያሾለከውን ኳስ ጨዋታው ላይ እድሎችን ያመከነው ማውሊ ቢያገኘውም ጨዋታው ላይ ጥሩ የነበረው እሌክስ አሙዙ ያዳነበትና ከቅጣት ምት ኦሰይ ማውሊ መትቶት ከግቡ እናት ለትንሽ ወጥቷል።በሁለተኛው እጋማሽ መከላከልን የመረጡት ባህርዳሮች ተቀይሮ በገባው ግርማ ዲሳሳ በኩል ያደረጉት ሙከራ ፊሊፕ ኦቮኖ መልሶባቸዋል። ሁለተኛው እጋማሽ ላይ ግብ እለማስተናገዱ ተከትሎ ጨዋታው በባህርዳር ከተማ እሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል።