የ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መዝጊያ ጨዋታ የነበረው የወልዋሎ እና የጅማ ኣባጅፋር ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።ወልዋሎ አዲግራት በ22ኛው ሳምንት ደደቢትን ካሸነፈው ቡድን ክርስቶፈር ችዞባን በአብዱራህማን ፋሱይኒ ሲቀይሩ ጅማዎች በበኩላቸው ሲዳማ ቡናን ከረታው ስብስብ 3 ቅያሬዎችን ማለትም ተስፋዬ መላኩን በኤልያስ አታሮ፣መስዑድ መሓመድን በብሩክ ገብረኣብ እንዲሁም ማማዱ ሲዲቤን በእክሊሉ ዋለልኝ ቀይረው ወደ ሜዳ አስገብተዋል።
የወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ ብልጫ በታየበት የመጀመርያ አጋማሽ በ4-2-3-1 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት ቢጫ ለባሾቹ በተሻለ መልኩ ወደ ግብ ቀርበዋል።ከሁለቱም መስመር በሚነሱ ኳሶች ማጥቃትን የመረጡት ወልዋሎዎች የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል።በፍጹም ቅጣት ሳጥን በግራ በኩል ኤፍሬም አሻሞ ያገኘውን ኳስ እንድ ተጨዋች በመቀነስ የሞከረው ኳስ ዘሪሁን ታደለ ይዟታል።በ4-5-1 አሰላለፍ መሃል ላይ ተጨዋቾችን በማብዛት የተጨወቱት ጅማዎች በተሻለ መልኩ ኳስን ማንሸራሸር ችለዋል።በ16ኛው ደቂቃ አስቻለው ከኦኪኪ አፎላቢ ጋር እንድ ሁለት ተጫውቶ ወደ ፍጹም ቅጣት ሳጥን ውስጥ ገብቶ በበረኛው አናት ለማሳለፍ የሞከረው ኳስ ከብዱላዚዝ ኬይታ አድኖበታል።በተጨማሪ ጅማ አባጅፋር በመላኩ ወልዴ እና በብሩክ ገብረኣብ ተጨማሪ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል።ወልዋሎዎችም በፕሪንስ ሰርቪንሆ ከቅጣት ምት ያደረጉት ሙከራ ለትንሽ ወደ ውጭ ወጥቷል ።በጨዋታው 28ኛው ደቂቃ ላይ አፍወርቅ ሃይሉ ከመሃል ሜዳ የላከው ኳስ አብዱራህማን ፋሱይኒ በሚገባ ተቆጣጥሮ ጅማ አባጅፋር መረብ ላይ አሳርፎ ወልዋሎን መሪ ማድረግ ችልዋል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ወልዋሎዎች ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ጅማዎች እቻ ለመሆን ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው የመጀመርያው እጋማሽ ተጠናቋል።
ሁለተኛው እጋማሽ ላይ ተሽለው የቀረቡት ጅማዎች ከቀኝ መስመር ዓወት ገብረሚካኤል በሚያሻግራቸው ኳሶች እድሎችን መፍጠር ችለዋል።በተለይ በ56ኛው ደቂቃ ዓወት ገብረሚካኤል ያሻማው ኳስ ኦኪኪ በግምባሩ የገጨው ካስ ተጣቃሽ ነው።ወልዋሎዎች በእንፃሩ በሁለተኛው እጋማሽ ወደ ኃላ በማፈግፈግ መልሶ ማጥቃትን ምርጫቸውን እድርገዋል።አክሊሉ ዋለልኝን በማማዱ ሲዲቤ፣ዲድዬ ሌብሪን በመስዑድ መሐመድ የቀየሩት ጅማዎች እጨዋወታቸውን ወደ 4-4-2 በመቀየር እድሎች መፍጠራቸው ማስቀጠል ሲችሉ ፣ የዚህ ጫና ውጤትም በ74ኛው ደቂቃ ላይ ደስታ ደሙ ኳስን በእጅ መንካቱን ተከትሎ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ኦኪኪ ኦፎላቢ እስቆጥሮ ጅማን እቻ ማድረግ ችሏል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ወልዋሎዎች ጨዋታውን ለማሸነፍ በደስታ ደሙ፣በራችሞንድ ኦዶንግ ያደረግዋቸው ሙከራዎች ሳይሳኩላቸው ጨዋታው በእቻ ውጤት ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
ውጤቱን ተከትሎ ጅማ እባጅፋር ነጥቡን 38 በማድረስ እምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልዋሎ 34 ነጥብ በመያዝ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።