በዮናስ ምስጋናው
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ወልድያ ከተማን ያስተናገደው ጅማ አባጅፋር በኦኮኪ አፎላቢ 64ደቂቃ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ ማሸነፍ ችሏል፡፡
በጨዋታው እንቅስቃሴ 10 ያህል ልጆችን በግል ና በጉዳት ምክንያት ያላካተተው ወልድያ አጠቃላይ ለጨዋታው 14 ልጆችን ብቻ ማስመዝገቡ እና ባሳለፍነው ረቡዕ ከመቀሌ ጋር ጨዋታ አድርጎ ከ3 ቀናት በሃላ መጫወቱ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴው ደካማ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ተመሳሳይ የ 4-4-2 አጨዋወት ይዘው የገቡት ሁለቱም ብድኖች አዝናኝ እግርኳስ ከመጫወት ይልቅ በመልሶ ማጥቃት ና የክንፍ ኳሶችን ለመጠቀም ሲሞክሩ ተስተውሏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በእለቱ ጨዋታውን ሲመሩ የነበሩት ዋና ዳኛ ኢብራሂም አጋዥ 5 የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመዙ 3ቱን ለጅማአባጅፋር እንዲሁም 2ቱን ለወልድያ ሰተዋል፡፡
በእለቱ ለጅማአባጅፋር የወልዲያ ተጫዋቾች ኳስ፡እዳይቆጣጠሩ እና ከአጥቂወች ጋር እዳይገናኙ በማድረግ ሲከላከሉ ቆይተዋል፡፡የጨዋታ ልዩነት የነበረው ከጅማ በኩል አማን ነስሩ የወልዲያ ከተማ የመሐል ክፍልን ኳሶችን በማጨናገፍ እና በመቁረጥ ትልቁ ድርሻ የነበረው ሲሆን ግዙፉን አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በሚገባ የተቆጣጠረው የወልዲያው ዳንኤል ደምሱ የጨዋታው ኮከብ ነበሩ፡፡
ጅማ አባጅፍር ውጤቱን ተከትሎ 3ደረጃ ሲይዝ ወልድያ 12 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ -ጅማ አባጅፋር
“ዛሬ ቡድናችን ተጭኖ በመጫወቱ አሸንፈን ወጥተናል፡፡ በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች በዚሁ የአሸናፊነት መንፈስ እንጫወታለን፡፡”
ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ -ወልዲያ ከተማ
” እንዳያችሁት ምንም ተጫዋች የለኝም 10 ያክል ተጫዋቾቼ በጉዳትና በተለያየ ምክኒያት አልነበሩም፡፡ በተቀያሪ ቦታ ላይ የነበሩት ሁለት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው የነበሩን” በተከታታይ 10 ቀናት 4ጨዋታዎችን እንድናደርግ መገደዳችን ተፅእኖ ፈጥሮብናል፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች ወደ አሸናፊነት እንመለሳለን”