በአፍሪካ ኮንፌደሬሺን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል ለመግባት በሚደረገው የ2ኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ የኮንጎውን ካራ ብራዛቪል ያስተናገዱት ፈረሰኞቹ በአዳነ ግርማ ብቸኛ ግብ ወደ ምድብ ድልድል አንድ እግራቸውን ያስገቡበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡
ፈረሰኞቹ በተጨዋች ጉዳት እና ቅጣት ምክንያት የተጨዋች የቦታ ሽግሸሽግ በማድረግ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን የግራ መስመር አጥቂውን ጋዲሳ መብራቴ ወደ መሃል አማካኝ ሲያመጡት የቡድኑ አንበል የሆነው ምንተስኖት አዳነ የመሃል ተከላካይነት ሚናን ሲወጣ ባመሸበት ምሺት በርካታ ተመልካች በአዲስአበባ ስታዲዬም ጨዋታውን ታድሟል፡፡
በጨዋታ ባለሜዳዎቹ አጥቅተው ጫና ፈጥረው ለመጫወት ሲሞክሩ እንግዳዎቹ ጥንቃቄን በመምረጥ ወደ ሇላ አፈግፍገው ሲከላከሉ አምሽተዋል፡፡በዚህም ባለሜዳዎቹ ቅዱስ ጊዬርጊሶች ገና በጨዋታው መጀመሪያ 7ኛውና 8ኛው ደቂቃ በሙሏለም እና አብዱልከሪም አማካኝነት ከሳጥን ውጭ የግብ ማግባት ሙከራዎችን ማድረግ ሲጀምሩ እንግዳዎቹ በመልሶ ማጥቃት የግብ ዕድል ለማግኘት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጉልህ የሚነሳ አልነበረም፡፡ባለሜዳዎቹ ፈረሰኞቹ በ16ኛው ደቂቃ በአንድ ሁለት ቅብብል ይዘውት የገቡትን ጥሩ ኳስ ጋዲሳ መብራቴ ሳይጠቀምበት መቅረቱ የሚያስቆጭ ሲሆን በ21ኛው ደቂቃ ፈረሰኞቹ በድጋሚ በግራ መስመር በመግባት በመሃሪ መና አማካኝነት ሌላ የግብ ሙከራ አድርገዋል፡፡
እንግዳዎቹ ካራ ብራዛቪሎች በመልሶ ማጥቃት በ30ኛው ደቂቃ ጥሩ ኳስ አግኝተው በቀላሉ ቢመክንም ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርጉ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ የማዕዘን ምት አግኝተው ነበር፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ በይበልጥ ተጭነው የተጫወቱት ባለሜዳዎቹ በ51ኛው ደቂቃ በበሃይሉ አሰፋ አማካኝነት ከርቀት ጥሩ ኳስ ወደ ግብ ሞክረው ለጥቂት የግቡ ቋሚ ለትሞ ሲመለስ በቅርብ የነበረው መሃሪ መና በድጋሚ ቢያገኘውም ኳሱን ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተውታል።እንግዳዎቹ በዚህኛው አጋማሽ በይበልጥ ወደ ሇላ ተመልሰው ግብ ላለማስተናገድ ሙሉ ለሙሉ መከላከል ላይ አመዝነው ሲጫዎቱ ባመሹበት በጨዋታው ፈረሰኞቹ ግብ ለማስቆጠር እንግዳዎቹ ካዛ ብራዛቪሎች ግብ ላለማስተናገድ በሚደረግ የጨዋታ መቆራረጥ ቀጥሎ ፈረሰኞቹ በድጋሚ በ65ኛው ደቂቃ ከመስመር በሀይሉ ያሻገረውን ኳስ አሜ መሀመድ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡በ69ኛው ደቂቃ ባለሜዳዎቹ ጋዲሳን መብራቴን በማስወጣት አዳነ ግርማን ቀይረው ወደ ሜዳ አስገብተዋል፡፡
ፈረሰኞቹ ግብ ለማግኘት ቀይረው ባስገቡት አዳነ ግርማ (ወፍጮው) አማካኝነት በበባሃይሉ አሰፋ ድንቅ ጥረት በረጅሙ ወደ ግብ ያሻገራትን ኳስ በጭንቅላቱ በመግጨት ፈረሰኞቹን መሪ ማድረግ ችሏል፡፡ከጎሏ መቆጠር በሇላ ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር የተንቀሳቀሱት ባለሜዳዎቹ በ82ኛው ደቂቃ አብዱልከሪም ኒኪማ አማካኝነት ለግብ የቀረበ ሙከራ ሲያደርጉ በ86ኛው በግብ አስቆጣሪው አዳነ ግርማ አማካኝነት ጥሩ የግብ ሙከራ በማድረግ ሌላ ግብ ሳይጨምሩ ጨዋታው በፈረሰኞቹ 1ለምንም አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
በዚህ ፈረሰኞቹ ምድብ ድልድል ውስጥ አንድ እግራቸውን አስገብተው ከ10 ቀን በሇላ ኮንጎ ላይ ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ ወደ ቦታው ያቀናሉ፡፡