በውበቱ አባተ መሪነት በዝውውሩ የመጀመርያ ሳምንታት በንቃት የተሳተፋት ሰበታ ከተማ ለመከላከያ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረውን አንተነህ ተስፋዬን አስፈርሟል።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንደማይሳተፋ ካረጋገጡ በኃላ ካስፈረሟቸው በርካታ ተጨዋቾች ጋር እየተለያዩ ሚገኙት መከላከያ ከድሬዳው ከተማ ካስፍረሙት አንተነህ ተስፋዬ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።ከዚህ ቀደም ለድሬዳዋ ከተማ፣ሲዳማ ቡና፣አርባምጭ ከተማ የተጫወተው አንተነህ በአሰልጣኝ አብርሃም መብራህቱም ጥሪ ተደርጎለት በብሄራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ ይገኛል።
ልምድ ያላቸው ብሀይሉ አሰፋ፣ዳዊት እስጢፋኖስ፣መስኡድ መሐመድ፣አስቻለው ግርማ ያስፈረሙት ሰበታ ከተማ በዘንድሮው ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል።