ሳምንታዊዋ፣ ተወዳጇና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገ ማክሰኞም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት በመቅረብ ልታስኮመኩሞት ከጫፍ ደርሳ በመጨረሻም ወደ ማተሚያ ቤት አምርታለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው የሀገር ውስጥ እትሟ ሄኒከን ቢራ ጥበባኛውን ሮናልዲኒሆን ወደ አገራችን በማስመጣት ከአድናቂዎቹ ጋር ሊያገኛኝ ከጫፍ ስለደረሰበትና መሰናዶውን ስላጠናቀቀበት ጉዳይ የሚወዱትን ዘገባ ይዛሎት የቀረበች ሲሆን ከእዚያ ውጪም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን አስመልክቶ ከሜዳው ውጪ ሲዳማ ቡናን በማሸነፍ ያልተጠበቀ ድል ስለቀናው የኢትዮጵያ ቡና ከክለቡ ተጨዋቾች ውስጥ አማካዩ ሳምሶን ጥላሁን ስላከናወኑት ጨዋታና ስለቡድናቸው በሊጉ ዋንጫ የማንሳት እድል አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን ሌላው ጋዜጣዋ ይዛ የወጣችው አነጋጋሪ መረጃ ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀይ መስቀል ዋና መ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘውንና ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር መ/ቤት በባለቤትነት እንዲያስተዳድር ኃላፊነት የተሰጠውን የኦይል ሊቢያ የነዳጅ ማደያ ጨረታ አስመልክቶ የጨረታውን ተሳታፊዎች ለሁለት ስለከፈለው ጉዳይ ይኸውም “የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነዳጅ ማደያውን የጨረታ ህጉን በጣሰ መልኩ መስጠቱ ውዝግብ አስነስቷል” በሚል የሠራነውን ዘገባ አስመልክቶ ለቀረበው ቅሬታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አቶ ዘላለም አይሸሹምና አቶ ጌታ ዘሩ ከዝግጅት ክፍላችን ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ቀርቧል፤ ሌላው በአሁን ሰዓት በጉዳት ላይ የሚገኘው የፋሲል ከተማውና የብሔራዊ ቡድናችን ተከላካይ የነበረው አይናለም ኃይሉ በእግር ኳሱ ዙሪያ አነጋጋሪ የሆነ ቆይታን ከጋዜጣው ጋር አድርጓል፤ ከእነዚያ ውስጥ ከተጨዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ አሰልጣኞች ሙስና ይሰራሉ የሚሉ አሉ… አንተ ጋስ መረጃ የለም በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ፣ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ፣ ስላጋጠመው ጉዳት፣ በፋሲል ከተማ ክለብ ዙሪያና ሌሎችንም ሊወዱት የሚችሉትን ምላሾች ሰጥቷል፤ ሀትሪክ ስፖርት ሌላ የነገ ዘገባዋ የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ አምድ እንግዳ አድርገን ያቀረብነው የአየር ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ድንቅ አጥቂ ኃይሉ ሰይፉን /ጎቢጥ/ ሲሆን ከእሱ ጋር ሰፊ ቆይታን አድርገናል፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿ ነገ ይዛሎት የምትቀርበው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች ማን ይሆናል? በሚለው ዘገባ ስለ ዴብሮይነ፣ ሞ.ሳላ እና ኬን የቀረበ ዳሰሳ ያለ ሲሆን የቀጣዩ የዝላታን ኢብራሂሞቪች ተተኪ ማነው በሚለው ዙሪያም ዘገባ ሊቀርብሎት ችሏል፤ ከእዚያ ውጪም ሌሎችም ሰፋፊ መረጃዎችን ከመዝናኛ አምዶቻችን ጋር ለእናንተ ሰፋ ያሉ መረጃዎችን አቅርበናል፡፡ ሀትሪክ የእናንተ ናት ይወዷታል፤ ያንብቧት
ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችንም ይዛሎት ቀርባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ
ሳምንታዊዋ፣ ተወዳጇና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ
Hatricksport team