በአለማችን ለመኖር፣ለመስራትና ለመማር ፍፁም ምቹና ተመራጭ ከሆኑት የአለማችን ምርጥ አራት ከተሞች አንዳ ተመራጭ ከተማ እንደሆነች የሚነገርላት የካናዳዋ ኦታዋ አንድ ታላቅ ድግስ ደግሳ እንግዶቻን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።
ላለፉት 365 ቀናት ወይም ለአንድ ዓመት ያህል በመላው አትሌቲክስ አፍቃሪያን በተለይ ደግሞ በካናዳዊያን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 43ኛው የኦታዎ ማራቶን በይፋ ሊጀመር ከ 24 ሠዓት ያነሰ ጊዜ ብቻ እንደቀረው ውድድሩን የደመቀ ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት የውድድሩ አዘጋጆች በዛሬው ዕለት ይሄንን የሁለት ቀናት ውድድር ለመዘገብ ከመላው ዓለም በመምጣት ኦታዋ ማዘጋጃ ቤት ለተሰባሰቡት ኢንተርናሽናል ጋዜጠኞች ይፋ አድርገዋል።
የኦታዋ ማራቶን በይፋ መከፈትን በይፋ ባበሰረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በስምዋ በተላከላት የቀጥታ ግብዣ ከኢትዮጵያ ሚዲያዎች በካናዳ ዋና ከተማ ማዘጋጃ ቤት በጋዜጣዋ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ በብቸኝነት ተወክላ የተገኘችው ሀትሪክ የስፖርት ጋዜጣ ውድድሩ ምን ያህል አለምአቀፍ ትኩረትን የሳበና ካናዳዊያን በተለይ የውድድሩ አስተናጋጅና ባለቤት የሆነችው ኦታዋ ነዋሪዎች ለውድድሩ ያላቸውን ከፍተኛ ቦታ በተግባር አይታ ለማረጋገጥ ችላለች።
ከከሚሊዮን ያነሰ ወደ 877ሺህ 300 ህዝብ ብቻ የሚኖርባት ግን የካናዳ አራተኛዋ ትልቅዋ ከተማ የሆነችው ኦታዋ
- ማሰታውቂያ -
በነገው ዕለት(ቅዳሜ)እና ከነገ በስቲያ (እሁድ) በሁለት ቀን ከምታካሂዳቸው ስድስት የስፖርት አይነቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የ10k እና የማራቶን ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ሁለቱም ርቀቶች በአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን(IAAF) የወርቅ ደረጃን በመያዝ በ10k በካናዳ ምድር የመጀመሪያ በአለም ደግሞ 4ተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
ዛሬ የመንግሥት መቀመጫና የተለያዩ ታሪካዊ ተቃማትና የቱሪስት መስህቦችና ሙዚየሞች መገኛ በሆነችው ኦታዋ ማዘጋጃ ቤት ሀትሪክን ጨምሮ ከመላው ዓለም ለተጋበዙ የሚዲያ ሠዎች በተሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኦታዋ ከንቲባን ጨምሮ የተለያዩ ታላላቅ ሠዎች የውድድሩን መከፈት በይፋ በሚያበስረው ሥነሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ኦታዋን በማስተዳደር ላይ የሚገኙት የ55 ዓመቱ ጎልማሳ James Alexander Watson(Jim)የኦታዋ ማራቶን በይፋ መከፈቱን ባበሰሩበት እንደተናገሩት “ካናዳውያን የ150ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን እያከበሩ ባለበት በዚህ ወቅት የኦታዋ ማራቶን መካሄዱ ውድሩን የተለ ያደርገዋል ያሉት ከንቲባው ንግግራቸውን ሲቀጥሉ”የኦታዋ ማራቶን ከውድድር ባለፈ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማገዝ፣ገንዘብ በማሰባሰብ(fund Raising)ለቻሪቲዎች በመስጠት በርካታ ቁም ነገር ያላቸውን ስራዎች የሚሡራ በመሆኑ አስተዋጽኦው ከፋተኛ ነው ያሉት ከንቲባው ውድድሩ ከማሸነፍ ጤናን ከመጠበቅ የዘለለ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዳለው ከንቲባው ተናግረዋል።
ከከተማዋ ከንቲባ James Alexander Watson Jim በተጨማሪ የጌትኒአ ከተማ ከንቲባ፣የከተማዋ ቱሪዝም ኃላፊ፣የውድድሩ ታይትል ስፓንሰር የሆነው Scotiabank ኃላፊና ሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች የኦታዋ ማራቶን የሩጫ ውድድር ብቻ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ከጋዜጣዊው መግለጫ በማስከተል ነገ(ቅዳሜ)በኢትዮጵያ ሠዓት አቆጣጠር እኩለ ቀን 6:00 ላይ የሚጀመረውን የ10ኪ.ሜ ውድድር አስመልክቶ ለአሸናፊነት ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው አትሌቶች ውድድሩን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ብዙም ያልተብራራ ግን አሸናፊነት ላይ ያጠነጠነ ምላሽ በአስተርጓሚያቸው በመታገዝ ሰጥተዋል።
ነገ ቅዳሜ በሚካሄደው የሴቶች የ10ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል 4 አትሌቶች ማለትም የሚሣተፉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ ተገኝተው አስተያየት ሰጥተዋል።