በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ የውድድር ዓመታቸውን ለማሳለፍ እየተዘጋጁ ሚገኙት ስሁል ሽረ የሃይለአብ ሃይለስላሰና ብሩክ ተሾመ ዝውውርን አጠናቀዋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከሻምፒዮኖቹ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው የትራንስ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቡድን ውጤት የሆነው የመሃል ሜዳ ተጨዋቹ ሃይለአብ የሳምሶን አየለን ስብስብ ተቀላቅሏል።መሀል ላይ የፈጣሪ ተጨዋች እጥረት የነበራቸው ስሑል ሽረ ሃይለአብን ማስፈረማቸው በመጠኑ ችግራቸውን ሊፈታላቸው አንደሚችል ይገመታል።የቀድሞው ዋልታ ፖሊስ፣መቐለ 70 አንደርታ፣ወልዋሎና ደደቢት ተጨዋች ሃይለአብ ከስሑል ሽረ ጋር ለቀጣይ ሁለት ዓመት ቆይታ ይኖረዋል።
ሌላ ስሑል ሽረን የተቀላቀለ ተጨዋች ብሩክ ሓዱሽ ነው።ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከሰበታ ከተማ ጋር የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ሻምፒዮን የሆነው ብሩክ በሁለት ዓመት ውል የቀድሞ ክለቡን ስሑል ሽረን ተቀላቅሏል።ከዚህ ቀደም ለፋሲል ከነማ፣ሰበታ ከተማ እና ስሑል ሽረ የተጫወተው ብሩክ ሓዱሽ የስሑል ሽረ የአጥቂ ክፍል ያጠናክራል ተብሎ ይገመታል።
- ማሰታውቂያ -
በተጨማሪ ስሑል ሽረ የሥስት ነባር ተጨዋቾቻቸው ክፍሎም ገብረሂወት ፣ሰይድ ሀሰን እና ሸዊት ዮውሃንስ ውል ሲያራዝሙ ከዲሜጥሮስ ወልደስላሴ ና ብሩክ ተሾመ ጋር ተለያይተዋል።