በሳምሶን አየለ ሚመሩት ስሑል ሽረ ወጣቱን የቀኝ ተመላላሽ መድሀንየ ብርሀነን በማስፈረም የክረምቱ ፈራሚዎቻቸውን ቁጥር 10 አድርሰዋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከታዩት ተስፈኛ ወጣቶች መሀከል በቅድሚያ ሚጠራው መድሀንየ በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር በንቃት እየተሳተፋ ሚገኙትን ስሑል ሽረን ተቀላቅሏል።ከደደቢት ታዳጊ ቡድን በ2010 ያደገው መድሀንየ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከደደቢት ጋር በግሉ የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል።
ከቀኝ መስመር ተከላካይነት በተጨማሪ በሁለቱም መስመር መጫወት ሚችለው መድሀንየ ከደደቢት ጋር ለመቆየት ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ከስሑል ሽረ ጠንከር ያለ ጥያቄ መምጣቱ ተከትሎ ከሰመያዊዎቹ ጋር በስምምነት መለያየት ችሏል።