በዮሴፍ ከፈለኝ
በሲዳማ ቡና የመሀል ክፍል ላይ
እንደፈለገ ሲፈነጭ ያዩት ቅዱስ
ጊዮርጊሶች ፈልገውታል… የእርሱም ልብ
ወደ ፈረሰኞቹ አዘንብሏል፡፡ ብዙዎቹ
ተጨዋቾች ጊዮርጊስ ሊገቡ ሲያስቡ ቅድሚያ
ምላሽ የሚፈልጉት ስለሚከፈላቸው
ደመወዝ ነው፡፡ ሙላለም መስፍን (ዴኮ)
ግን እንዲህ አልነበረም.. መጫወት
እንደሚፈልግ በመግለፅ የመጫወትን እድል
በሚገባ አገኛለሁ ወይ አለ እንጂ ስንት
ትከፍሉኛላችሁ አላለም…ጊዮርጊሶች በም/ል
አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታ አማካይነት
አናገሩትና ለፈረሰኞቹ ፊርማውን አኖረ…
አሁን በየጨዋታው የፈረሰኞቹን ማሊያ
ለብሶ እየተጫወተ ነው፡፡ በ2011 ፕሪሚየር
ሊግ ከ3 ጨዋታ ሁለቱን መሸነፋቸውን
ተከትሎ ዴኮ ከዮሴፍ ከፈለኝ ለቀረበለት
ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ፡- ኪሎ ቀነስክ እንዴ?
ሙላለም፡- (ሳቅ) አዎ ቀንሻለሁ….ወደ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስመጣ 81 ወይም 82 አካባቢ
ነበርኩ ትንሽ ቆይቶ ኪሎዬ በ3 ጨምሮ ወደ
85 አካባቢ ደርሶ ነበር አሁን ግን ወደ80
ኪሎ ተመልሻለሁ
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ
የምትለው ምኑን ነው?
ሙላለም፡- ይሄ ነው ብዬ መናገር ወይም
አጨዋወቱ እንዲህ ነው ማለት ይቸግረኛል..
አምና ኳስ ይዘን ለመጫወት ስንሞክር ነበር
አሁን ደግሞ በረጃጅም ኳሶች እየተጫወትን
በመስመር በሚሄዱ ኳሶች ማጥቃትን
የሚመርጥ አጨዋወት ተከትለናል
ሀትሪክ፡- ክለቡን ከተቀላቀልክ ጀምሮ
የገረመህ የትኛው ነገር ነው?
ሙላለም፡- ደጋፊው ነዋ! ይሄ
ደጋፊ የሚያስገርም ሆኖ ብኛል
በነሱም ደስተኛ ነኝ
ሀትሪክ፡- ከ3 ጨዋታ 2
ሽንፈት አይከብድም?
ሙላለም፡- በጣም ከባድ
ነው እንኳን ለጊዮርጊስ
ለሌላውም ክለብ ከባድ ነው
ጥሩ ስሜት አልፈጠረብንም
በጣም አዝነናል በቀጣይ ግን
መሪውን ሃዋሳን አሸንፈን
ለማገገም እንሞክራለን ብዬ
አስባለው
ሀትሪክ፡- ሽንፈቱ የመጣው በጊዮርጊስ
ድክመት ወይስ በተጋሚዎቹ ጥንካሬ?
ሙላለም፡- ሽንፈቱ የመጣው በጊዮርጊስ
መድከም እንጂ በሌሎቹ ክለቦች መጠናከር
አይደለም፡፡
ሀትሪክ፡- የአሰልጣኞች መቀያየርስ
ተጽዕኖ የለውም?
ሙላለም፡- አለው እንጂ…በተወሰነ
መልኩ ተጽዕኖ መኖሩ የግድ ነው ምክንያቱም
አምና ሙሉ ስንሰራበት የነበረ ሲስተም አለ
አሁን ደግሞ ወደ ሌላ ሲሰተም እየሄድን
ነውና ችግርማ ይኖረዋል….ይሄ ደግሞ ከባድ
ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ከሲዳማ ቡና ጋር ስትጫወቱ
2 ጎል የሚሆኑ ኳሶችን እንደሳትክ ሰማሁ
እውነት ነው?
ሙላለም፡- አዎ ስቻለሁ…የመጀመሪያው
ለመሳት የሚከብድ ኳስ ነው የሳትኩት…
በረኛው ነው የያዘብኝ የውሳኔ ችግርም
ነበረብኝ የቱ ጋ መምታት እንዳለብኝ
አልወሰንኩም ነገር ግን በረኛው ይወድቃል
ብዬ በቴስታ ስመታው ቆሞ ጠበቀኝና
ያዝብኝ፡፡ ሁለተኛውንም ኳስ በቴስታ
መታሁት በረኛው አዳነብኝ በሁለቱም
ኳሶች በረኛውን ማድነቅ ብቻ ነው
የሚቻለው… እርሱን አለማድነቅ
አይቻልም?
ሀትሪክ፡- ጊዮርጊስ ዋንጫ
የሚበላው በዳኛ ነው የሚባል አባባል
ነበር፤.. አሁንስ ይሄን አየህ?
ሙላለም፡- ፈፅሞ ውሸት ነው
በፍፁም ይሄን አላየሁም ሌላ ቡድን
እያለው የማስበው እንደዚህ ነበር
አሁን ግን በተቃራኒ ዳኞች ሁሉ
ጊዮርጊስን ሲጫኑ ነው ያየሁት ይህን
ስል የጊዮርጊስ ተሰላፊ ስለሆንኩ
አይደለም፡፡ በፊት የሰማሁትና አሁን
ያየሁት ፍፁም የተራራቀ ነው
አይገናኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ላንተ ለዋሊያዎቹ
መጫወት ወይስ ለጊዮርጊስ መጫወት
ነው ጫና ያለው?
ሙላለም፡- ያለምንም ጥርጥር
ለጊዮርጊስ መጫወት ነው ጫና
ያለው፡፡ ለብሔራዊ ቡድን ስጫወት
ብዙ የማያሸንፍ ብዙ ጊዜም
የሚሸነፍ በመሆኑ ብዙም ጫና የለም
ጊዮርጊስ ጋር ግን ሁሌም ማሸነፍ
የተለመደበት ክለብ በመሆኑ ጫናው
ይከብዳል ብሔራዊ ቡድን ቶሎ ቶሎ
አትጫወትም ጊዮርጊስ ጋር ግን
በየሳምንቱ መጫወት ስላለ ጫናው
ከፍተኛ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ለጊዮርጊስ ከፈረምክ
በኋላ ካገባሃቸው ጎሎች ምርጡ
የትኛው ነው?
ሙላለም፡- ኢትዮጵያ ቡና ላይ
ያገባሁት ምርጡ ጎሌ ናት፡፡
ሀትሪክ፡- ለደጋፊዎቹ የምትለው
ቃል አለ?
ሙላለም፡- በውጤቱ ቅር
መሰኘታቸውን እናውቃለን… ከአዋሳ
ከተማ ጋር በምናደርገው ቀጣይ
ጨዋታ በግሌም ሆነ እንደቡድን
እንክሳቸዋለን ብቻ ነው ማለት
የሚቻለው፡፡ በደንብ እንደምናሸንፋቸው
ርግጠኛ ነኝ ድጋፋቸው አይለየን ነው
ማለት የምችለው፡፡ ሀ