“ለአገር ስፖርት ትልቅ ውለታን የዋለው የባንክ እግር ኳስ ክለብ በመፍረሱ
ስሙ የሚነሳበትንና የሚታወስበትን ሐውልት በአቅሜ ለማቆም እየጣርኩ ነው”
ሸዋረጋ ደስታ (የቀድሞ የባንኮች ተጨዋች)
በይስሐቅ በላይ
ቀደም ሲል የባንኮች ስፖርት ክለብ
እየባለ በሚጠራበት ጊዜ ዘጠኝ አመታት
የክለቡን ማልያ ለብሶ የተጫወተው፤
በድንገት ከጨዋታ በተገለለበት ወቅት
ደግሞ የባንኮች ስፖርት ክለብን በቴክኒክ
ኮሚቴ ሰብሳቢኒትና በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
አባልነት፤ በሀገር ደረጀ ደግሞ የኢትዮጵያ
እግር ኳስ ፌዴሬሽን በብሔራዊ የቴክኒክ
ኮሚቴ አባልነት ያገለገለውና በስፖርት
ቤተሰቡ ዘንድ ተለይቶ የሚታወቀው ሸዋረጋ
ደስታ “የባንክ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ
ፕሮጀክት” በይፋ አቋቋመ፡፡
“በኢትዮጵያ እግር ኳስ የ40 ዓመታት
የገዘፈ ታሪክ ያለው ታላቁ የንግድ ባንክ እግር
ኳስ ክለብ በ30 ደቂቃ ጋዜጣዊ መግለጫ
እንዲፈርስ የተወሰነበት ውሳኔ በውስጤ
የማያባራ ቁጭትና እልህን በመፍጠሩ
ይሄ ለሀገር ስፖርት ትልቅ ውለታን የዋለ
ክለብ በመፍረስ ታሪክ ሆኖ ከሚቀር ስሙ
የሚነሳበትንና የሚታወስበትን ሀውልት
በአቅሜ ለማቆም አንዲሁም ለእውቅና
ያበቃኝንና የምወደውን እግ ኳስ ዳር ሆኜ
ከመውቀስና ከመተቸት በዘለለ ለምን ለእድገቱ
የራሴን ጡብ አላስቀምጥም ከሚል ቀና
አስተሳሰብ በመነጨ የባንክ እግር ኳስ ክለብ
ማሰልጠኛ ፕሮጀክትን በይፋ አቋቁሜያለሁ”
በማለት የሚናገረው የቀድሞው ባለውለተኛ
ተጨዋች ሸዋረጋ ደስታ ከአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የስፖርት ማህበራት ማደራጃ አስፈላጊውን
መስፈርት በማሟላት የምስክር ወረቀትና
እውቅና እንደተሰጠውና ይሄንንም ተከትሎ
ህልሙን እውን ለማድረግ በይፋ እንቅስቃሴ
መጀመሩን በተለይ ለሀትሪክ ገልጿል፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ቁጭትና እልህ
የውስጤን ሰላም በመንጠቃቸውና የሀገሬን
እግር ኳስ በአቅሜ ለማገልገል ነው “የባንክ
እግር ኳስ ክለብ ማሠልጠኛ ፕሮጀክት”ን
በይፋ ያቋቋምኩት የሚለውን ሸዋረጋ ደስታን
ሃሳቡ እንዴት ሊጠነሰስ ቻለ…?ግቡስ
ምንድነው? ሲል ከዚህ በታች ባለው መልኩ
ጠይቆታል፡፡
ሀትሪክ፡- በዚህን ሰዓት የባንክ እግር ኳስ
ክለብ ማሰልጠኛ ፕሮጀክትን የማቋቋም ሃሳቡ
እንዴት መጣ?
ሸዋረጋ፡- ይሄ ፕሮጀክት ቁጭት የወለደው
የማሰልጠኛ ፕሮጀክት ነው፤ በኢትዮጵያ
እግር ኳስ ትልቅ ታሪክ ያለው የባንክ እግር
ኳስ ቡድን በ30 ደቂቃ መግለጫ የ40 አመት
ክለብ ፈርሶ ወደ ታሪክነት መቀሩ የክለቡን
ማልያ ለብሶ እንደተጫወተ፣ ለውጤታማነቱ
እንደደማ ሰው ህሊናዬ ውሳኔውን በፀጋ
መቀበል አልቻለም፤ ይልቁንም እንደ እግር
ውስጥ እሳት እየለበለበ ሰላሜን ነጠቀኝ፡፡
ክለቡን ከመፍረስ መታደግ አለብኝ በማለት
ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ የስፖርት ቤተሰቦችን
ፊርማ (ፔትሸን) በማሰባሰብ በወቅቱ የባንኮች
ኃላፊ ወደነበሩት የተከበሩ አቶ በረከት ስሞኦን
ድረስ ይዤ በመሄድ አቤት ብል፣ በተለያዩ
ሚዲያዎች ጩኸቴን የብዙዎችን
ጥያቄ ባሳማም ጆሮ የሚሰጠኝ
በማጣቴና ክለቡን ከመፍረስ መታደግ
ባለመቻሌ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ
በሚል ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- ምን… ለማድረግ…?
ሸዋረጋ፡- የእኔም ሆነ የብዙዎች
ጩኸት ከንቱ ሆኖ መቅረቱንና
ክለቡ መፍረሱ ለማመን የሚክበድ
እውነት መሆኑ ሲረጋገጥ “እልህ ምላጭ
ያስውጣል” እንደሚባለው ይሄ ለሀገር እግር
ኳስ ብዙ አስተዋፅኦ ያደረገ ክለብማ በነበር
የሚነሣ ታሪክ ብቻ ሆኖ መቅረት የለበትም
በሚል በአቅሜ ሁሌም ስሙ የሚነሣበት
የሚታወስበት ሐውልት በአቅሜ ማቆም
አለብኝ፤ እግረ መንገዴንም የሀገሬን እግር
ኳስ ማገዝ አለብኝ በሚል ቀና ስሜትን
በመጨመር የባንክ እግር ኳስ ማሰልጠኛ
ፕሮጀክትን በይፋ አቋቋምኩ፡፡
ሀትሪክ፡-አሁን “የባንክ እግር ኳስ
ማሰልጠኛ ፕሮጀክት” በይፋ ተቋቁሟል ማለት
ነው…?
ሸዋረጋ፡- አሁን ከአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት
ማህበራት ማደራጃ ፈቃድ በ23/02/11 በአቶ
ገ/ህይወት ገ/ስላሴ በሚባሉ ኃላፊ ተፈርም
የምስክር ወረቀትና አውቅና ተሰጥቶኛል፤
በቀጣይ ደግሞ የማሰልጠኛ ፕሮጀክቱ በይፋ
መመስረትን አስመልክቶ በማዘጋጀው ደማቅ
በዚህ ስርዓት ሥራችንን በይፋ መጀመራችንን
እናበስራለን፡፡
ሀትሪክ፡- የባንክ እግር ኳስ የማሰልጠኛ
ፕሮጀክት አመስራረቱ እንዴ ነው
ሸዋረጋ፡- የሃሳቡ አመንጪና ባለቤቱ
እኔው ነኝ፤አመሰራረቱና አወቃቀሩም በቦርድ
ደረጃ የሚመራ ነው፤ የያዝኩትን የተቀደሰ
ዓላማ በማየት በቦርድ አባልነት የሚሰሩ
ታላላቅ ሰዎች አብረውኝ አሉ፡፡ ስማቸውን
ለመጥቀስ ያህል አቶ ፍቅሩ ተፈራ (የቦርድ
ሰብሳቢ)፣ አቶ በድሩ ሙዘይን፣ ዶ/ር አያሌው
ጥላሁን፣ ወ/ት አሰለፈች ደስታ፣ አቶ እሸቱ
ከበደ፣ አቶ ፋሲል ገሠሠ እና አቶ ይስሀቅ
በላይ በአባልነት ተካተውበታል፡፡ ሁሉም
ለአግር ኳስ በጣም ቅርብ የሆኑ የሀገራቸው
እግር ኳስ አለማደግ የሚያንገበግባቸው ቅን
አሳቢዎች የተዋቀሩበት ቦርድ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የባንክ እግር ኳስ ማሰልጠኛ
ፕሮጀክት ትኩረት የሚያደርገው በየትኛው
የእድሜ እርከን ላይ ነው…?
ሸዋረጋ፡- – -አሁን እንደመነሻ ከ17 አመት
በታች በሆኑ ታዳጊዎች ላይ ነው ስልጠናውን
ለመጀመር ያሰብነው፤ በቀጣይ ግን ከ13 እና
ከ15 አመት በታች ታዳጊዎች ላይ ከሥር
የምንሰራ ነው የሚሆነው፡፡ በነገራችን ላይ
እኛ ይሄን ሃሳብ ስናስብ ከሀብታም ልጆች
ገንዘብ የመሰብሰብ ግብን ይዘን አይደለም፤
ከገንዘቡ ይልቅ ትኩረት የምንሰጠው ለታለንት
ነው፡፡ የእግር ኳስ ታለንት ኖሮአቸው ጎዳና
ላይ ቤንዚን እየሳቡ ምፅዋት የሚለምኑ
ሕፃናትንም የምንመለምልበት መንገድንም
ዘርግተናል፡፡
ሀትሪክ፡- ሙያተኞችን በተመለከተስ ምን
ያህል አስበህበታል?
ሸዋረጋ፡- አንድ የማሰልጠኛ ፕሮጀክት
ሊኖረው የሚገባው ባለሙያ እንዲኖረው
አድርገን ነው የቀረፅነው፤ እየሰራንም
ያለነው፡፡ ሙያተኛን በተመለከተ የሚገርምህ
ታላላቅና በሕፃናት ላይ የተሻለ እውቀት
ያላቸው ሙያተኞችን በሁሉም ዘርፍ አካተን
ይዘናል፡፡ የሚገርምህ ግን ገና ከወዲሁ እንደ
ወርቁ ደርገባ አይነት ታላላቅ አሰልጣኞች በበጎ
ፈቃደኝነት እናገለግልሃለን ከጎንህ ነን እያሉኝ
ነው፤ በዚህ ደስ ብሎኛል፡፡ ከዚህ ውጪ
በህክምናው፣ በስልጠናው፣ በውጪ ግንኙነት፣
በስነ ልቦናና በትምህርት ላይ አቅሙ ያላቸው
ሰዎች የተሰባሰቡበት ነው፡፡
ሀትሪክ፡-የማሰልጠኛው የገቢ ምንጭ
ምንድነው…? በባለሀብቶችና ስፖንሰሮች
የሚደገፍ ነው.. ?
ሸዋረጋ፡- እውነት ለመናገር ይሄን
ሃሳብ ወደ እውነትነት ለመቀየር ብዙ
ደክሜያለሁ፤ እስከአሁን ሁሉንም ውጪ
የምሸፍነው ከቤተሰቦቼ አፍ እየነጠኩ በግሌ
ነው፡፡ ሃሳቡን ስጠነስሰውም ድጋፍ እናገኛለን
የሚል ስሌትንም ሰርቼ አይደለም፡፡ ወደፊትም
በዚሁ መንገድ እንቀጥላለን ብዬም ነው
የማምነው፡፡ ነገር ግን የማሰልጠኛ ፕሮጀክቱን
መቋቋም የሰሙ ወዳዶቼ ከወዲሁ ከጎንህ ነን፤
ምን እናግዝ? በሚል አጋርነታቸውን እያሳዩኝ
ነው፡፡ ይሄ ደግሞ አስቤ ለተነሣሁት አላማ
ትልቅ ጉልበት ሆኖኛል፡፡ በተለይ የባንክ
እግር ኳስ ማሰልጠኛ ፕሮጀክት እውቅና
ማግኘትን በፌስ ቡክና በተለያየ መንገድ
የሰሙ ሁሉ በተለይ ከባህር ማዶ ከአሜሪካ
ከካናዳና ከአውሮፓ ጭምር የታላቁ ክለብ
ስም እንዲነሣ ላደረከው ጥረት ደስ ብሎናል፤
በርታ እናግዝሃለን በማለት ትልቅ የሞራል
ስንቅ እየሰጡኝ ነው፡፡ በዚህም ብዙ የሃሣቤ
ደጋፊዎችና አጋሮች እንዳሉኝ አረጋግጫለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት
የነበረው ሂደትና ውጣ ውረድ ምን ይመስላል…
?ጥረትህን በማገዝ በኩልስ ከወዲሁ የተባበሩህ
አሉ…?
ሸዋረጋ፡- መድገም እንዳይሆንብኝ እንጂ
የማሰልጠኛ ፕሮጀክቱን ለማቋቋም ብዙ
ለፍቻለሁ፤ በባንክ እግር ኳስ ክለብ መፍረስ
ያጣሁትን እንቅልፍና ሰላሜን ለመመለስ ብዙ
ደክሜ አሁን ትንሽ ተንፈስ ብያለሁ፡፡የነበረው
ውጣ ውረድ ቀላል የሚባል አልነበረምና ከጎኔ
በመሆን ያገዙኝን በሙሉ በተለይ ሌት ተቀን
አብረውኝ የደከሙትን የቦርድ አባላቶቼን፣
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ለትብብራቸው አመሰግናለሁ፡፡ ከመጀመሪያ
እስከ መጨረሻ ከጎኔ ያልተለየኝና ትልቅ
ዕገዛ ያደረገልኝ አቶ አሌክሳንደር ንጉሴና
የንግድ ባንክ ምክትል አሰልጣኝ የነበረውን
ሲሳይን እንዲሁም የባንኮች ስፖርት ማህበር
ስራ አስኪያጅ አቶ አስናቀ…..ን፤ ከሁሉም
በላይ ደግሞ ከፍ ያለ ምስጋና ማቅረብ
የምፈልገው ወደ ቢሮአቸው በሂድኩበት
ጊዜ ከመቀመጫቸው ተነስተው በመቀበል
ይዤ ለተነሳሁት አላማ ክብርና ድጋፋቸውን
ያለስስት የሰጡኝን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ምክትል ፕሬዝዳንትና የስፖርት ማህበሩ
ፕሬዝዳንት የሆኑትን አቶ አሊ መሐመድን
በራሴና በቦርድ አባላት ስም አመስግናቸዋለሁ፡
፡ አቶ አሊ በሜዳ ብቻ ድጋፍ ብቻ ሳንወሰን
በሌሎችም ድጋፎች ከጎነህ እንሆናለን
በማለትም ትልቅ የሞራል ስንቅ ስለሰጡኝ
እሳቸውን ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ሙያተኞችን በተመለከተስ ምን
ያህል አስበህበታል?
ሸዋረጋ፡- አንድ የማሰልጠኛ ፕሮጀክት
ሊኖረው የሚገባው ባለሙያ እንዲኖረው
አድርገን ነው የቀረፅነው፤ እየሰራንም
ያለነው፡፡ ሙያተኛን በተመለከተ የሚገርምህ
ታላላቅና በሕፃናት ላይ የተሻለ እውቀት
ያላቸው ሙያተኞችን በሁሉም ዘርፍ አካተን
ይዘናል፡፡ የሚገርምህ ግን ገና ከወዲሁ እንደ
ወርቁ ደርገባ አይነት ታላላቅ አሰልጣኞች
በበጎ ፈቃደኝነት እናገለግልሃለን ከጎንህ ነን
እያሉኝ ነው፤ በዚህ ደስ ብሎኛል፡፡ ከዚህ
ውጪ በህክምናው፣ በስልጠናው፣ በውጪ
ግንኙነት፣ በስነ ልቦናና በትምህርት ላይ
አቅሙ ያላቸው ሰዎች የተሰባሰቡበት ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በቀጣይ ፕሮጀክቱ
በይፋ ሲጀመር ሰፋ ያለ ቃለ-ምልልስ
እንደሚኖረን ተስፋ እያደረኩ በቅርቡ
መፅሐፍ እንደምታስመረቅ በይፋ ሲነገር
ሰምቻለሁ፤ መፅሐፍህ ከምን ደረሰ የሚለው
የመለያያ ጥያቄያችን ቢሆንስ…?
ሸዋረጋ፡- – ለሰጠኸኝ እድል በቅድሚያ
አመሰግናለሁ፤ ቀደም ሲል እግር ኳስ
እርዳታና ስፖርት የሚለውን የበኩር
መፅሐፌን በአቅሜ አበርክቼያሁ፤ አሁን
ግን እንዳልከው “የክለቦች ህብረትና የእግር
ኳስ ፌዴሬሽኑ ውዝግብ እውነታዎች”
እውነተኛ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ታሪክ
ላይ የሚያጠነጥነው መጽሐፌ ተፅፎ
ሁሉም ነገር ተጠናቋል፤ አሁን የማሰልጠኛ
ፕሮጀክቱን ፈቃድ የማስጨረስ ጉዳይ
ስለያዘኝና ፕሮጀክቱንም መጽሐፉንም አንድ
ላይ ለማስመረቅና ይፋ ለማድረግ በመወሰኔ
መጽሐፉ ትንሽ ዘግይቷል አሁን ግን
ሁሉም ነገር በመጠናቀቁ ሁለቱም ታላላቅ
እንግዶች የስፖርት ቤተሰቦች የሚዲያ ሰዎች
በተገኙበት በቅርቡ ይፋ ይሆናል፡፡