ወደ ድሬድዋ ያቀናው ቅዱስ ጊዬርጊስ ከሜዳው ውጭ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያለ ግብ በአቻ ውጤት ነጥብ ተጋርቷል፡፡
በኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ የሁለተኛው ዙር 16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ስታዲዬሞች ከተካሄዱ 7 ጨዋታዎች በብቸኝነት ግብ ያልተስተናገደበት የድሬዳዋ ከተማና ቅዱስ ጊዬርጊስ ጨዋታ ከቀኑ 9:00 ሲል በድሬዳዋ ስታዲዬም የጀመረውን ይሄንኑ ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ኢንተርናሺናል ዳኛ በላይ ታደሰ የመሩት ሲሆን ጨዋታው ከመጀመሩ አስቀድሞ ለቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ ተጨዋች የነበረውና አሁን በህይወት ለሌለው ለናትናኤል ሞገስ የህሊና ፀሎት በማድረግ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡
በጨዋታው ባለሜዳዎቹ ድሬድዋ ከተማዎች በ15ኛው ሳምንት አዲስአበባ ስታዲዬም በኢትዮ ኢለክትሪክ 1ለ ምንም ሽንፈትን ካስተናገዱበት 11የመጀመሪያ ተሰላፊዎች በዛሬው ጨዋታ የ3 ተጨዋቾችን ለውጥ አድርገዋል፡፡ያሬድ ዘውድነህን ቀይሮ ዘነበ ከበደ ሲገባ ፡በኢማኑኤል ላሪያ በረከት ይሳቅ እንዲሁም ሙየዲን ሙሳ ቀይረው ሀብታሙ ወልዴን በማስገባት ገብተዋል፡፡
እንግዳው ቅዱስ ጊዬርጊስ በ15ኛው ሳምንት በሀዋሳ ከተማ 4ለ1 ሽንፈትን ባስተናገደበት ጨዋታ ቋሚ 11 ተሰላፊዎች ከነበሩት የ4 ተጨዋቾችን ለውጥ ሲያደርግ፡ግብ ጠባቂውን ኦዶንካራ ለአለም ተክቶት ሲገባ በተከላካይ ክፍሉ መሀሪ መና ምንተስኖት አዳነን ቀይሮት ገብቷል፡በሌላ በኩል በአብዱልከሪም መሀመድ ምትክ ፍሬዘር ሲገባ ጋዲሳ መብራቴን በአማራ ማሌ በመቀየር ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡አማራ ማሌ በዚህ ጨዋታ የመጀመሪያውን የሊግ ጨዋታ በቋሚ አሰላለፍ ተጫውቷል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በዚህ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ተመጣጣኝ የሚባል እንቅስቃሴ የነበረበት ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ድሬዎች በካውንተር አታክ የግብ ዕድል ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ እንግዳዎቹ ፈረሰኞቹ ኳስን ከተከላካይ መስመር መስርተው የግብ ዕድል ለመፍጠር ሲጫዎቱ ፡ከባለሜዳዎቹ ድሬዎች ቀድመው የግብ ሙከራ ያደረጉት ፈረሰኞቹ ነበሩ፡፡በጨዋታው መጀመሪያ በ5ኛው ደቂቃ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊግ ጨዋታ ወደ ሜዳ በገባው አማራ ማሌ አማካኝነት የግብ ሙከራ ሲያደርጉ በዚሁ አጋጣሚ የተጨረፈው ኳስ ለገዬርጊሶች የመጀመሪያ የማዕዘን ምት ሁኖል፡፡የማዕዘን ምቱ ሲሻገር የድሬዳዋ ተጨዋቾች ኳሱን ተቆጣጥረው በመልሶ ማጥቃት ጥቃት ሲሰነዝሩ በ6ኛው ደቂቃ የማዕዘን ምት አግኝተዋል፡፡
በጨዋታው እስከ 16 ኛው ደቂቃ ድረስ መሃል ሜዳ ላይ በሚደረግ ትንቅንቅ ግልፅ የጎል ዕድል ሁለቱም በኩል ባይፈጥሩም በዚሁ ደቂቃ ፈረሰኞቹ በአማራ ማሌ አማካኝነት አንድ ለአንድ ይሄው ተጨዋች ከድሬዳዋው ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሳው ጋር ቢገናኝም ሳይጠቀምበት ሲቀር ፈረሰኞቹ በ20ኛው ደቂቃ በአቡበከር ሳኒ ድንቅ አጨራረስ ኳስና መረብን ቢያገናኙም ከጨዋታ ወጭ በሚል ግቧ ስትሿር፡
ባለሜዳዎቹ ድሬዎች የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ከመመከት ባለፈም በ20ኛው ደቂቃ በግራ መስመር በኩል በአንድ ሁለት ቅብብል ሰብረው በመግባት ወደ ግብ የተሻገረው ኳስ ለትንሺ በግቡ አግዳሚ መውጣቱ በትንሹም ቢሆን የአጠፋውን ምላሽ ለመስጠት የታሰበ ሙከራ ነበር፡፡
ብዙም ሳይቆዩ ፈረሰኞቹ በተመሳሳይ በዚሁ በ20ኛው ደቂቃ ፈረሰኞቹ በመልሶ ማጥቃት በፍሬዘር ካሳ አማካኝነት በመስመር በኩል የግብ ዕድል ቢፈጥሩም በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ጀማል ኳሷን በቀላሉ መያዝ ችሏል፡፡ከዚህኛው ደቂቃ ጀምሮ እስከ 39ኛው ደቂቃ ድረስ በሁለቱም በኩል የጠራ የግብ ዕድል መፍጠር ባይችሉም በ40ኛው ደቂቃ ፈረሰኞቹ ከማዕዘን ያሻገሩትን ኳስ አዳነ ግርማ በግንባሩ ገጭቶ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጭ የወጣበት ተጠቃሺ ሙከራ ነበር፡፡
ቅዱስ ጊዬርጊሶች በሁለተኛው አጋማሽ አዳነ ግርማን ቀይረው ታደለ ምህረቴን ወደ ሜዳ በማስገባት ግብ ለማግኘት ብዙ ቢደክሙም፡ባለሜዳዎቹ ድሬዎች አለመጠቀማቸው እንጂ በ79 ኛው ደቂቃ የጠራ የግብ ዕድል መፍጠር ችለው ነበር፡፡ከዚህኛው ደቂቃ በውላ እንግዳዎቹ ጊዬርጊሶች የማሸነፊያ ግብ ለማግኘት ወደ ድሬ የግብ ክልል ተጠግተው ጫና ለመፍጠር ሲጫዎቱ ባለሜዳዎቹ የአቻነቱን ውጤት ላለማጣት የግብ ክልላቸውን አጠረው ተከላክለው ወተዋል፡፡ጨዋታው ዛሬ ከተካሄዱ 7ጨዋታዎች ብቸኛው ግብ ያልተሰተናገደበት ጨዋታ ሁኖ ሲመዘገብ ፡ፈረሰኞቹ አቻ በመውጣታቸው በደረጃ ሰንጠረዡ 1 ደረጃ ዝቅ ብለው በ24 ነጥብ 6ኛ ላይ ሲቀመጡ፡፡ባለሜዳዎቹ ድሬዎች በ14 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዘው ወራጂ ቀጠና ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡
☞ስምኦን አባይ-ድሬድዋ ከተማ
በጨዋታው ጥሩ ተጫውተናል፡፡ በርካታ የግብ እድሎችን ፈጥረናል አለመጠቀማችን ግን ወጋ የሚያስከፍልነው፡፡ተጨዋቾቸ ለማሸነፍ ከነበራቸው ፍላጎት አንፃር ይመስለኛል ኳሶች ባክነዋል፡፡አሁን ግን የማስበው ስለ ቀጣዩ ጨዋታ ነው፡፡
☞ቫስ ፒንቶ-ቅ/ጊዬርጊስ
በ እንቅስቃሴ ሁለታችንም ጥሩ ነበርን፡፡ የተጫዋቾችን ከጉዳት አለመመለስ ቡድናችን ላይ ክፍት እንዳለ ተመልክተናል፡፡በቀጣይ ያሉብንን ክፍተቶች ሞልተንወደ አሸናፊነት እንመለሳለን፡፡
Photo credit-የፈረሰኞቹ ገጽ