በ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ መርሀ ግብር ቀጥሎ ሲደረግ በቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ከሜማሎ ሰንዳውንስ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታ ኘሪቶሪያ ላይ እሚያደርገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ ላይ በሰልሀዲን ሰኢድ ብቸኛ ጎል አሸንፏል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታውን በ4-3-3 ቅርፅ አሰለፉን ሲጀምር በአንፃሩ ጅማ አባቡና በ4-5-1 ቅርፅ ወደ ሜዳ ሲገቡ ጨዋታው በተጀመረ በ13ኛ ደቂቃ አሜ መሀመድ በግራ መስመር ብቻውን የተቆጣጠረው ኳስ ከጨዋታ ውጭ አቋቋም ላይ ነህ በሚል የመስመር ዳኛው ሲያስቆሙት ብዙም ሳይቆይ በ13ኛ ደቂቃ ላይ ከደጉ ደበበ ጎን ለጎን ሮጦ ያገኛትን ኳስ ለጥቂት ሮበርቶ ኦዶንካራ ሲያዳነበት ፡፡ በ21ኛ ደቂቃ ላይ 27ቁጥሩ ነተንቢ ክርዚስቶም ከመሀል ሜዳ መሬት ለመሬት የመታት ኳስ የጎሉን ጠርዝ ታካ ወጣለች፡፡በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በ22ኛ ደቂቃ ላይ ሰላዲን በርጌቾ ከመሀል መዳ የዟት የሄደውን ኳስ ወደ ጎል ሞክሮት ጀማል ጣሰው ሲተፋበት ጎል ስር የነበረው ሰላዲን ሰይድ በድጋሜ ሞክሮ ጀማል ጣሰው በአስደናቂ ሁኔታ ከጎልነት አድኖታል፡፡ በጨዋታው በ31ኛ ደቂቃ አዳነ ግርማ መሀል ሜዳ ላይ አክርሮ የመታው ኳስ ጀማል ጣሰው በሚገርም ሆኔታ ያዳነበት እሚጠቀስ ነው፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱ ክለቦች በኩል እሚጠቀሱ ሙከራዎች ነበሩ፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ በ52ኛ ደቂቃ ላይ ተስፋዬ አለባቸው ከ ጀማል ጣሰው ጋር በፈጠሩት መጎሳሰም የመሀል ደኛው ተስፋዬ አለባቸውን በቀይ ካርድ ከሜዳ አሰናብተዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በ54ኛ ደቂቃ ላይ ሳላሃዲን ሰኢድ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግንባር በመግጨት ከመረብ አሰርፎ ቅዱስ ጊዮርጊስን መሪ ሲያደርግ ለራሱ በሊጉ 15ኛ ጎሉን አስቆጥሯል ፡፡
ከጎል መቆጠረ በኅላ ጅማ አባ ቡና ደጋፊዎች ቁሳቁስ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ሲወረውሩ ተያይቷል፡፡
በጨዋታው በ70ኛ እና በ73ኛ ደቂቃ ላይ ዳዊት ተፈራ አክርሮ የመታት ኳስ በጎሉ አናት ሲስዳት ብዙም ሳይቀይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ጎል ክልል ውስጥ አስቻለው ያአስቀረበት እሚጠቀስ ነው፡፡ ከሁለተኛው አጋማሽ በኃላ ከባድ ዝናብ ሲጥል በሁለቱም ክለቦች የተጫዋቹ ቅያሪ ሲደረግ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በ74ኛ ደቂቃ ፕሪንስ ወጥቶ ራምኬሎ ሎክ ;እዲሁም በ 88ኛ ደቂቃ ላይ አዳነ ወጥቶ አብደልከሪም ገብተዋል፡፡በጅማ አባቡና በኩል ነተንቢ ወጥቶ ቢንያም እንዲሁም ሄኖክ ወጥቶ ቴድሮስ አስገብተዋል፡፡
ጨዋታው ሊጠናቀቅ 5ደቂቃ ሲጨመር በ91ኛ ደቂቃ ላይ ጅማ አባቡናዎች የመአዘን ኳስ አጊንተው ሳይጠቀሙበት ቀርተው ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ከጨዋታው መጠናቀቀ በኃላ በስታዲየሙ በደጋፊዎቻቸው መከላከል ስርአት አልበኝነት ተይቷል፡፡
pic-credit የፈረሰኞቹ ገጽ
ደረጃ ሰንጠረዥ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 26 | 24 | 52 |
2 | ደደቢት | 27 | 16 | 48 |
3 | ሲዳማ ቡና | 27 | 9 | 47 |
4 | ኢትዮጵያ ቡና | 27 | 11 | 44 |
5 | አዳማ ከተማ | 27 | 8 | 44 |
6 | ፋሲል ከተማ | 26 | -1 | 38 |
7 | መከላከያ | 27 | -8 | 35 |
8 | ሀዋሳ ከተማ | 27 | 1 | 34 |
9 | ወልዲያ ከተማ | 27 | -1 | 33 |
10 | አርባምንጭ ከተማ | 27 | -3 | 32 |
11 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 27 | -2 | 29 |
12 | ወላይታ ድቻ | 26 | -10 | 29 |
13 | ጅማ አባቡና | 27 | -5 | 28 |
14 | ድሬዳዋ ከተማ | 27 | -10 | 28 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
27 | -13 | 25 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 26 | -16 | 19 |