ሰርቢያዊውን ሰርዳን ዚቮጅሆቭ በዋና አስልጣኝነት የቀጠሩት ፈረሰኞቹ የክረምቱ አምስተኛ ፈራሚያቸውን አይቮሪኮስታዊውን ዛቦ ቴጉይ ዳኒን አድርገዋል።ባሳለፍነው ዓመት አጋማሽ የስዋዚላንዱን ማንዚኒን በመልቀቅ የጋናውን ኣሻንቲ ኮቶኮቶን በ3 ዓመት ውል የፈረመው ዛቦ ቴጉይ ከስምንት ወራት በኃላ ቀዮቹን በመልቀቅ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ ዓመት ውል መፈረሙን የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ አድሬስ ገልጽዋል።
በርካታ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋቾች ያሉት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛቦ ቴጉይን ማስፈረሙን ተከትሎ በቀጣይ ዓመት ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ሚኖረውን ፋክክር ከወዲሁ አጓጊ ያደርገዋል።