ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል
በሀገር ውስጥ ዘገባችን የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንግዳችን ናቸው…. ” በአሰልጣኝ ውበቱ ድል አሰልጣኝ አብርሃምም ይሞገስ ማለት ቸልሲ ባሳካው የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ከቶማስ ቱሄል ጋር ላምፓርድም ይሸለም እንደማለት እንዳይሆን እሰጋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ባህሩ “የተቀመጥኩበት ወንበር እስካሁን አልቆረቆረኝም እንደ እሳትም አልፈጀኝም” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
*….የኢትዮዽያ ቡናው አማኑኤል ዮሃንስ “ጥሩ ጎናችን የያዝነውን አጨዋወት አለመልቀቃችን ነው…ያም ነው ለኮንፌዴሬሽን ካፑ ያሳለፈን” ሲል ተናግሯል።
- ማሰታውቂያ -
*… የታዋቂው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም ሊካሄድ ነው….ሁሉም ከባለውለተኛው ጎን እንዲቆም ተጠይቋል። ዝግጅቱን ከሚመሩት ኮሚቴዎች መሃል አቶ ኢሳያስ ደንድርና አቶ አብዱረህማን መሃመድ / አቡሽትን/ አነጋግረናቸዋል።
*…. ሰበታ ከተማ በቀድሞው ግብ ጠባቂው ዳንኤል አጄ ተከሷል…. ፊፋም በ45 ቀን ውስጥ ቀሪ የ600 ሺህ ብር ደመወዙን ክፈሉ ብሎ አስጠንቅቋል።…
*.. ሀድያ ሆሳዕናም ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎበት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ጸንቷል….
*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….
*….. ከብዙ ወራቶች ጉጉት በቅርብ ጊዜያት በኋላ ከተካሄደ እልህ አስጨራሽ ድርድር በኋላ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ተረቷል…ኮከቡን ጄደን ሳንቾን ወደ 73 ሚሊዮን ፓውንድ በሚጠጋ ሂሳብ ለማን.ዩናይትድ አስረክቧል… በዚህ ዝውውር ዙሪያ ያዘጋጀነው ዘገባ አለ…..
*…” አርሰናልን መቀላቀሌ በብዙ መልኩ እንዳድግ አድርጎኛል” ሲል የግራ መስመሩ ፈጣን ኬረን ቴርኒ አስተያየቱን ሰጥቷል …..
*….ከእውሮፓ ዋንጫው የተሰናበተው ፖል ፖግባ ሀዘኑ የበረደ አይመስልም…”አንዳንዴ እግርኳስ ጨካኝ መሆኗን አውቄያለሁ” ሲል ሃዘኑን ገልጿል….
*…. ራሂም ስተርሊንግ የዩሮ 2020 ምርጡ ይሆን? ምላሹን ልዩ ዘገባው ላይ ያገኙታል..
*…..የአውሮፓ ዋንጫና ሌሎች የዝውውር ዜናዎችን አካተናል……
እናም ሌሎች መረጃዎች….
እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..
ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……