መቐለ 70 እንደርታ ከ አዳማ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ታህሳስ 29/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ
ቦታ: ትግራይ ስታድየም
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 7ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከልደት በዓል ማግስት ቀጥሎ ሰባት ጨዋታዎችን ያስተናግዳል።መቐለ ላይ የውድድሩ የአምናው ሻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ አደማ ከተማን ሚያስተናግድ ይሆናል።ከቀኑ 9 ሰዐት ሲል ሚጀምረውን ጨዋታ በዚህ መልኩ ዳስሰነዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት የደረሰባቸው መቐለ 70 እንደርታዎች አንጋፋ ተጨዋቻቸውን ሚኪኤለ ደስታን አሁንም በጉዳት ማያሰልፋ ይሆናል።ፈረሰኞቹን በገጠሙበት ዕለት ደካማ እንቅስቃሴን ያሳዩት ምዐም አናብስቶቹ ቀዋሚ 11 ተሰላፊዎች ላይ ለውጦችን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይገመታል።በሜዳቸው በሚያደርጉዋቸው ጨዋታዎች ላይ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው መጫወትን ተመራጭ ሚያደርጉት መቐለዎች በዛሬው ጨዋታም ተመሳሳይ አጨዋወትን ይዘው ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በያዝነው ውድድር አመት ምንም ሽንፈትን ያላስተናገዱት አዳማዎች በበኩላቸው ሚካኤል ጆርጅ እና ብሩክ ቃልቦሬን በጉዳት ማያሰልፋ ይሆናል።ባሳላፍነው ሳምንት ከጅማ አባጅፋር ጋር ነጥብ የተጋሩት አዳማዎች በአብዛኛው መከላከል ላይ ትኩረት አድርገው በመልሶ ማጥቃት እድሎችን ለማግኘት ይሞክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።በተለይ ፊት ላይ ሚያሰልፍዋቸው ፈጣን ተጨዋቾች አጨዋወቱን መተግበር ላይ ከባድ ሀላፊነት ሊሰጣቸው እንደሚችል ይገመታል።