የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ (ቅዳሜ) አንድ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን ነገ (እሁድ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ሲዳማ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ሲዳማ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ
የጨዋታ ቀን: እሁድ ጥር 03/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ወልዴ ንዳው
የጨዋታ ቦታ: ይርጋለም ስታዲየም
የስምንተኛው ሳምንት ከሚያተናግዳቸው ሌላኛው ተጠባቂ መርሀ ግብር ይህ ዋነኛው ነው።
ሲዳማ ቡና በአስፈሪው የፊት መስመሩ ማለት በአዲስ ግደይ ፤ ሀብታሙ ገዛኸኝ እና ይገዙ ቦጋለ እየተመሩ ጥሩ ጅማሮን ማድረግ ቢችሉም ባለፉት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ በተከታታይ ነጥብ እየጣሉ ይገኛሉ።
ሁለቱ ቡድኖች በስምንተኛው ሳምንት ሲገናኙ በሁለት ነጠቦች ብቻ ተራርቀው ነው ፡፡ በተለይም ደግሞ በሊጉ የነጥብ መቀራረበች ይበልጥኑ ለሊጉ ድምቀት ሰጥቶት ታይቷል ፡፡
ባህር ዳር ከተማ በአዲሱ አሰልጣኛቸው ፋል ተካልኝ እየተመሩ በሊጉ ጥሩ ጉዞን እያረጉ ይገኛሉ ፡፡ በተለይም በሁለቱ ቡድኖች መካከል ከሚጠበቀው ብረቱ ፉክክር አንዱ የሁለቱም ቡድኖች የፊት መስምር ጥንካሬ አንደኛው ነው ፡፡
ለተመልካች አዝናኝ እንደሚሆን በሚጠበቀው በዚህ መርሀ ግብር ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች ድል የሚቀናቸው ከሆነ በአስራ ሁለት ነጥብ በሊጉ ሶስተኛ ላይ የሚያስቀመጣቸውን ውጤት የሌሎችን ቡድኖች ውጤት ጠብቀው የሚቀመጡ ይሆናል ፡፡
በሌላ በኩል ባህርዳር ከተማዎች ድልን የሚጎናፀፉ ከሆነ በአስራ አራት ነጥብ የሌሎች ክለቦችን ነጥብ መጣል ጠብቀው የሊጉ መሪ እስከ መሆን የሚያስችላቸውን ደረጃ ያገኛሉ።