የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በበአል ሰሞን የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ (ማክሰኞ) አንድ እንዲሁም ነገ (ረቡዕ) ደግሞ ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ሰባት ጨዋታዎች መካከል ባህርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ባህርዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ታህሳስ 29/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር በላይ ታደሰ
የጨዋታ ቦታ: ባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ላይ የደረሰ ሲሆን በዚህ ዙርም በውድድር አመቱ ጥሩ ወጣ ገባ የሚል አቋም እያሳየ የሚገኘው ባህርዳር ከተማ በሜዳው ባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ የሚገኘውን ኢትዮጵያ ቡናን የሚያስተናግድ ይሆናል። በዘንድሮው የውድድር ዘመን ሁለቱም ቡድኖች ከሜዳቸው ውጪ ማሸነፍ የሚቸገሩ ቡድኖች ሲሆኑ እስካሁን ከሜዳቸው ውጪ ምንም ድል ማስመዝገብ አልቻሉም።
ባህርዳር ከተማ እስካሁን ካደረጋቸው 6ጨዋታዎች ሁለቱን በሜዳው ያደረገ ሲሆን ሁለቱንም ጨዋታዎች ሲያሸንፍ 7ግቦችን አስቆጥሮ 3ግቦች አስተናግዷል። ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ በ6ሳምንታት ከሜዳው ውጪ 3ጨዋታዎችን ሲያደርግ በአንዱ ተሸንፎ በሁለቱ አቻ መውጣት ሲችል በነዚህ 3ጨዋታዎች 2ግብ ሲቆጠርበት 1ግብ አስቆጥሮ ተመልሷል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በባህርዳር ከተማ ከባድ ፈተና የሚገጥመው ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
በ6ኛው ሳምንት ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ወደ ጎንደር ተጉዞ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም በፋሲል ከነማ የ3-0 ሽንፈት አስተናግዶ ሲመለስ ኢትዮጵያ ቡና በአንፃሩ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሀዲያ ሆሳዕናን ገጥሞ 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፎ ወደ መሪዎቹ መጠጋት ችሏል። ይህንንም ተከትሎ ባህርዳር ከተማ በ8ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ ቡና ከተጋጣሚው ባህርዳር ከተማ በ1ነጥብ ከፍ ብሎ በ9ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በነገው ጨዋታ የሚሸናነፉ ከሆነ የደረጃ ለውጥ የሚከሰት ይሆናል። ኢትዮጵያ ቡና በጨዋታው ድል የሚቀናቸው ከሆነ የሌሎች ቡድኖች ነጥብ መጣልን ጠብቀው በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ የመቀመጥ እድልን የሚያገኙ ይሆናል። ባህርዳር ከተማ ድል የሚያስመዘግቡ ከሆነ ከኢትዮጵያ ቡና በላይ መቀመጥ ሲችሉ በሌሎች ቡድኖች ውጤት ላይ ተመርኩዞ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ይችላሉ።
ይህ ቅድመ ዳሰሳ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በባህርዳር ከተማ በኩል የተሰማ የጉዳት ዜና የሌለ ሲሆን
በኢትዮጵያ ቡና በከል ታፈሰ ሰለሞን ከነገው ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።